በዓለም ፡ ጨለማ ፡ እውር ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ
አንድ ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ዓይኔን ፡ ከፍቶት ፡ አየሁ (፫x)
አንድ ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ዓይኔን ፡ ከፍቶት ፡ አየሁ
ብርሃኔ ፡ ተገፎ ፡ በዓለም ፡ ስደናቀፍ
ዓይኔን ፡ ከፈተልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥሙ ፡ ይክበር (፫x)
ዓይኔን ፡ ከፈተልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ሳሙ ፡ ይክበር
ከጉዳት ፡ የሚያድን ፡ መሪ ፡ እንኳን ፡ ሳይንረኝ
አንድ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ እረዳት ፡ ሆነልኝ (፫x)
አንድ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ እረዳት ፡ ሆነልኝ
ከጥንት ፡ ከበፊቱ ፡ እውር ፡ እንደነበርኩ
አሁን ፡ ግን ፡ እንደማይ ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ ፡ ሥሙ ፡ ይክበር (፪x)
አሁን ፡ ግን ፡ እንደማይ ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ
ከሸንጐም፡ ብወጣ ፡ በማንም ፡ ብጠላ
ጌታን ፡ አመልካለሁ ፡ የሕይወቴን ፡ ከለላ (፫x)
ጌታን ፡ አመልካለሁ ፡ የሕይወቴን ፡ ከለላ
ጠቃሚና ፡ ጐጂውን ፡ የማላውቅ ፡ ለይቼ
ብርሃኔ ፡ ተገልጦ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ አይቼ (፫x)
ብርሃኔ ፡ ተገልጦ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ አይቼ