Mihretihin Ayichalehu (ምህረትህን ፡ አይቻለሁ)

አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ (፪x)

አስራ ፡ ሁለት ፡ ዓመት ፡ ደም ፡ እየፈሰሰኝ
ተነጥዬ ፡ መኖር ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ እራቀኝ
ከእንግዲህስ ፡ ወዲያ ፡ ተስፋዬ ፡ ምንድን ፡ ነው
ዕድሜዬ ፡ በሙሉ ፡ በለቅሶ ፡ ሊያልቅ ፡ ነው
ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ሃሳቤን ፡ ስጠብቀው ፡ ፍጻሚዬን
ድንገት: ብርሃን: ወጣልኝ: አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ መጣልኝ

አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ

ግርግሩ ፡ በዝቶ ፡ የሚጋፋው ፡ ሰው
አዳኜ ፡ ኢየሱስን ፡ እንዴት ፡ ላግኘው
ተስፋ ፡ ባለመቁረጥ ፡ እየተንፉቀኩኝ
እጄን ፡ ሰደድኩና ፡ ቀሚሱን ፡ ነካሁኝ
ነካ ፡ ባደርገው ፡ ነካኝ ፡ ኃይልም ፡ ወጣና ፡ ዳንኩኝ
ታዲያ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ አመስግኑልኝ ፡ በልልታ

አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ

ዘመናት ፡ አለፉ ፡ ሆኜ ፡ በጭንቀት
ለደሜ ፡ ማድረቂያ ፡ ጠፍቶ ፡ መድሐኒት
ማንም ፡ ማይጠጋኝ ፡ እርኩስ: ናት: ተብዬ
አሁንስ ፡ መረረኝ ፡ ገላግለኝ ፡ ጌታዬ
ብዬ ፡ ሞቴንም ፡ ስናፍቅ ፡ በሽታዬ: አርጎኝ: ድቅቅ
መሲሁ ፡ መጣልኝና ፡ አቆመኝ ፡ ፈወሰኝና

አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ

ትድናለች ፡ ብሎ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ገመተኝ
ሁሉም ፡ በሩቅ ፡ ሲሸሽ፡ ጀርባውን ፡ ሲሰጠኝ
አስታማሚ ፡ አጥቼ ፡ የምደግፈኝ
ኢየሱስ ፡ ሲጐበኘኝ ፡ በዛ ፡ ሚያጅበኝ
የሸሹኝ ፡ ሁሉ ፡ አቀፉኝ፡ የናቁኝ ፡ ሁሉ ፡ አከበሩኝ
መሸማቀቄም ፡ ቀረልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ይመስገንልኝ

አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x)
ምህረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ አወራለሁ
ምሕረትህን ፡ አይቻለሁ ፡ ዘምራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ አወራለሁ
ማዳንህን ፡ ቀምሻለሁ ፡ ዘምራለሁ

حال ہی میں سنا

0 تبصرے
    کوئی تبصرہ نہیں ملا

:: / ::
::
/ ::

قطار