ሠማያቶች ፡ ይስሙ ፣ ይስሙ ፡ ምድር ፡ ታስተጋባ
የምቀኘውን ፡ ቅኔ ፡ ያለኝን ፡ ምሥጋና
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፣ ፍሬ ፡ በፊቱ ፡ ላፍስሰው
ትናንት ፡ እንዳዜምኩት ፡ ደስታዬ ፡ በአንተው ፡ ነው
በአንተ ፡ የታሰበ ፡ የተረዳ ፡ ሰው
ጌታ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው (፪x)
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ክብር ፡ ያየው
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ወግ ፡ ያየው
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ደስ ፡ ያለው
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ክብር ፡ ያየው
እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው ፡ ወግ ፡ ያየው (፪x)
በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፣ ሁሉ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ አወራለሁ
ስላደረክልኝ ፡ ድንቅ ፡ ቆሜ ፡ ዘምራለሁ
ከአደረከው ፡ አንዳች ፣ አንዳች ፡ አልጐደለብኝም
ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ አንተስ ፡ እስከ ፡ ለዘለዓለም
በአንተ ፡ የታሰበ ፡ የተረዳ ፡ ሰው
ጌታ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው (፪x)
እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ክብር ፡ ያየው
እንደ ፡ እኔስ ፡ ማነው ፡ ወግ ፡ ያየው (፮x)