Ruth Tadesse Amesgenhalew (አመሰግናለው)

አዝ:- አመሰግናለው (፪x)
ያረክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው
የሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው

ሕይወትን ፡ ሰጥተኀኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞትክና
ዋጋዬን ፡ ከፈልክልኝ ፡ አስታረቅከኝ ፡ ከአብ ፡ ጋር
በኀጢአት ፡ የጠፋውን ፡ ያጣሁትን ፡ ማንነቴን
አገኘሁት ፡ በአንተ ፡ ሆነኅልኝ ፡ መስዋእቴ

ሚስጥርህን ፡ ገለጥክልኝ ፡ መጥተህ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ
ኢየሱሴን ፡ አምኜው ፡ ወስኜ ፡ ስቀበል
ከዛ ፡ ቃልህን ፡ ከፍቼ ፡ መረዳት ፡ ስጀምር
ለእኔ ፡ ያሰብከው ፡ ሁሉ ፡ ይገለጥልኝ ፡ ጀመር

አዝ:- አመሰግናለው (፪x)
ያረክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው
የሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው

እንዴት ፡ ብዬ ፡ ዝም ፡ ልበል ፡ አስቸገረኝ ፡ መደበቁ
የበራልኝ ፡ እውነት ፡ እኮ ፡ ያስገርማል ፡ ከሌሎቹ
እንዴትስ ፡ ይደበቃል ፡ ኧረ ፡ መቼ ፡ ተችሎ
ለብዙዎች ፡ ሚስጥር ፡ ሲሆን ፡ ሳየው ፡ ለእኔ ፡ ግን ፡ ተገልጦ

አዝ:- አመሰግናለው (፪x)
ያረክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው
የሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው

የበላይ ፡ እግዚአብሔር ፡ የለም ፡ አንተን ፡ ሚመስልህ
ገና ፡ እስከዘለዓለም ፡ አንተ ፡ ትመለካለህ
አመታት ፡ ተሰጥተውኝ ፡ ብናገር ፡ ብጨምር
እንዴት ፡ ብዬ ፡ አውርቼ ፡ ስለአንተ ፡ ልፈጽም

አዝ:- አመሰግናለው (፪x)
ያረክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው
የሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው

최근에 들은 사람

0 코멘트
    댓글이 없습니다

:: / ::
::
/ ::

대기줄