Eysus Tikekel (ኢየሱስ ፡ ትክክል)

አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድልም
ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገል ፡ ብታድን
ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል
አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል (፪x)

የበጐቹ ፡ መብዛት ፡ የላሞች ፡ መርባት
የርሻው ፡ መብልን ፡ መስጠት ፡ ጐተራው ፡ መሙላት
ሁሉም ፡ ተስብስቦ ፡ ቢከብ ፡ በዙሪያዬ
የሚያህልህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድል
ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገል ፡ ብታድን
ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል
አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል

መለኪያዬ ፡ ችግር ፡ እይደለም ፡ ማጣት
ወይ ፡ አግኝቶ ፡ መክበር ፡ ምድራዊ ፡ ሃብት
ለእኔ ፡ ሚበጀውን ፡ ከአንተ ፡ ይልቅ ፡ ማን ፡ ያውቃል
ነፍስን ፡ ከመስጠት ፡ ሁሉስ ፡ መች ፡ ይበልጣል

አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድልም
ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገል ፡ ብታድን
ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል
አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል

ብሩንና ፡ ወርቁን ፡ ዓለምስ ፡ መች ፡ አታ
እርካታ ፡ አጣች ፡ እንጂ ፡ ሰጭውን ፡ እረስታ
ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ
ቢሞላ ፡ ቢጐድል ፡ ሆንክልኝ ፡ ደስታ

አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድልም
ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገል ፡ ብታድን
ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል
አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል

የጸሎቴ ፡ መልሱ ፡ ቢዘገይም ፡ ፈውሴ
አንተ ፡ ካየህልኝ ፡ ተስማማሁ ፡ ኢየሱሴ
በጨለማው ፡ ስልጣን ፡ ጭንቅላት ፡ ላይ ፡ ቁሜ
እባርክሃለሁ ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ

አዝ፦ ቢመች ፡ ባይመች ፡ ቢሞላ ፡ ቢጐድልም
ብትሰጥ ፡ ብትከለክል ፡ ብትገድል ፡ ብታድን
ሥም ፡ አወጣሁልህ ፡ ብዬ ፡ ትክክል
አሜን ፡ ጌታ ፡ ትክክል

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue