Eregnan Yeqebal (እረኛን ፡ ይቀባል)

ሳሙኤልም ፡ ወደ ፡ ሳኦል ፡ መጣ
ሳኦልም ፡ አንተ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ የተባረክ ፡ ሁን
የእግዚአብሔርን ፡ ትዕዛዝ ፡ ፈጽሜአለሁ ፡ አለው
ሳሙኤልም ፡ ይህ ፡ በጆሮዬ ፡ የምሰማው ፡ የበጐች ፡ ጩኸትና
የበሬዎች ፡ ግሳት ፡ ምንድን ፡ ነው? አለ
ሳኦልም ፡ ህዝቡ ፡ ለአምላክህ ፡ ይሰውአቸው ፡ ዘንድ
መልካሞቹን ፡ በጐችና ፡ በሬዎችን ፡ አድነዋቸዋልና
አማሌቃዊያንም ፡ አምጥተዋቸዋል
የቀሩትንም ፡ ፈጽመን ፡ አጠፋን ፡ አለው
ሳሙኤልም ፡ ለሳኦል ፡ አለቀሰ
እግዚአብሔርም ፡ በእስራኤል ፡ ላይ ፡ ሳኦልን ፡ ስላነገሠ ፡ ተጸጸተ

እስከመቸ ፡ ድረስ ፡ ለሳኦል ፡ ታለቅሳለህ
ውረድ ፡ ቤተልሔም ፡ በቀንድ ፡ ዘይት ፡ ሞልተህ
ከልጆቹ ፡ መሃል ፡ አዘጋጅቻለሁ
ወደ ፡ እሰይ ፡ ቤት ፡ ግባ ፡ ንጉስ: እቀባለሁ
ሲለኝ ፡ አግዚአብሄር ፡ ፈራሁ ፡ ተደናገጥሁ
ሳኦል ፡ እንዳይሰማ ፡ ብዬ ፡ እጅጉን ፡ ፈራሁ
አንዲት ፡ ጊደር ፡ ይዤ ፡ ጌታዬ ፡ እንዳዘዘኝ
ጠራሁት ፡ እሰይን ፡ ልጆቹን ፡ እንዲያሳየኝ

በእውነት ፡ መልኩ ፡ ያማረ ፡ ቁመናው ፡ ሸበላ
ወደእኔ ፡ የተጠጋ ፡ ኤልያብ ፡ ነው ፡ ለካ
እግዚአብሔር ፡ ሚቀባው ፡ በፊቴ ፡ ይህ ፡ አለ
ለእስራኤል ፡ ንጉሥ ፡ ኧረ ፡ እፎይ ፡ ተገኘ
ብዬ ፡ በውስጤ ፡ አስቤ ፡ ልቀባው ፡ ስጠጋ
እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ፡ አትቸኩል ፡ በል ፡ ረጋ
ሰው ፡ ፊትን ፡ እንደሚያይ ፡ እኔ ፡ አላይምና
በዓይኔ ፡ ፊት ፡ ቀሏል ፡ አልያብን ፡ አትቀባ (፪x)

ሌሎችም ፡ ሰባቱ ፡ አለፉ ፡ በፊቴ
እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ አለኝ ፡ አልመረጥኩም ፡ እኔ
ልጆቹም ፡ አለቁ ፡ ማን ፡ ይሆን ፡ የቀረው
የሚቀባው ፡ የታል: ሰዉን: ግራ ፡ ገባው
የቀረ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ እነዚሁ ፡ ናቸው
እስኪ ፡ እሰይ ፡ ልጆችህን ፡ በደንህ ፡ ቁጠራቸው
ገና ፡ ታናሽ ፡ አለ ፡ በጐች ፡ የጠብቃል
አለኝ ፡ መለሰና ፡ ሥሙ ፡ ዳዊት ፡ ይባላል (፪x)

ተጠርቶ ፡ መጣና ፡ በእኔ ፡ ፊት ፡ ቆመ
እግዚአብሔርም ፡ አየው ፡ ዓለኝ ፡ ቀባው ፡ ሂደህ
የአምላኬ ፡ መንፈስ ፡ ወደደው ፡ አረፈበት
ዳዊት ፡ ያ ፡ እረኛው ፡ በእውነት ፡ አማረበት

እግዚአብሔር ፡ ለካስ ፡ መቼ ፡ ፊትን ፡ ያያል
ልቡን ፡ ከወደደ ፡ እረኛን ፡ ይቀባል
እኔም ፡ ታሪክ ፡ አለኝ ፡ የዳዊትን ፡ መሳይ
አምላኬ ፡ ከትቢያ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ ሲያነሳኝ
እግዚአብሔር ፡ ለካስ ፡ መቼ ፡ ፊትን ፡ ያያል
ልቡን ፡ ከወደደ ፡ ምስኪኑን ፡ ያከብራል
እኔም ፡ ታረክ ፡ አለኝ ፡ የዳዊትን ፡ መሳይ
አምላኬ ፡ ከትቢያ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ ሲያነሳኝ

በሰው ፡ ዓይን ፡ ሲታዩ ፡ ዓይን ፡ የሚሞሉ
ትከሻቸው ፡ ሰፊ ፡ ቁመናቸው ፡ ብቁ
አልጠፉም ፡ ብዙ ፡ አሉ ፡ አገሩን ፡ ሞልተዋል
በጊዜ ፡ . (3) . እንጂ ፡ ታዲያ ፡ መች ፡ ከብረዋል

ለምን ፡ እንደወደደኝ ፡ በውል ፡ ባይገባኝም
ስለእራሴ ፡ ማውቀው ፡ ውብ ፡ ታሪክ ፡ የለኝም
እንደ ፡ እስራኤል ፡ በዕፍረት፡ ነበርኩ ፡ እራቁቴን
ኢየሱሴ ፡ መጥቶ ፡ ጠጋ ፡ ባያለብሰኝ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ለካስ ፡ መቼ ፡ ፊትን ፡ ያያል
ልቡን ፡ ከወደደ ፡ እረኛን ፡ ይቀባል
እኔም ፡ ታረክ ፡ አለኝ ፡ የዳዊትን ፡ መሳይ
አምላኬ ፡ ከትቢያ ፡ ከአመድ ፡ ላይ ፡ ሲያነሳኝ

最近收听的

0 注释
    没有找到评论

:: / ::
::
/ ::

队列