ማን ፡ ያንከባለው ፡ ይህን ፡ ድንጋይ
ብዬ ፡ ስማትር ፡ ታች ፡ ላይ
ቀና ፡ ብዬ ፡ እንዳይ ፡ አደረከኝ
ለካስ ፡ ተንከባሏል ፡ ያስጨነቀኝ (፪x)
አሻቅቦ ፡ ማየት ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ
አድርጎኛል ፡ ጌታ ፡ ችግርን ፡ እንዳላይ
ሻገር ፡ ሻገር ፡ ብሎ ፡ አይኔ ፡ ከሩቅ ፡ አይቶ
ያመሰግንሃል ፡ ሁሉን ፡ በአንተ ፡ ረስቶ (፪x)
ይኸው (፬x)
ጌታ ፡ ተቀበለው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው
ጌታ ፡ ተቀበለው ፡ አምልኮዬ ፡ ይኸው (፪x)
ጭንቅ ፡ ጥብብ ፡ ወየው ፡ ያልኩበት
አንገት ፡ ያስደፋኝ ፡ ያለቀስኩበት
ያኔ ፡ ያስፈራራኝ ፡ ልቤን ፡ ያራደው
ተንከባለለ ፡ ከፊቴ ፡ ያለው (፪x)
አሻቅቦ ፡ ማየት ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ
አድርጎኛል ፡ ጌታ ፡ ችግርን ፡ እንዳላይ
ሻገር ፡ ሻገር ፡ ብሎ ፡ ዓይኔ ፡ ከሩቅ ፡ አይቶ
ያመሰግንሃል ፡ ሁሉን ፡ በአንተ ፡ ረስቶ (፪x)
ይኸው (፬x)
ጌታ ፡ ተቀበለው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው
ጌታ ፡ ተቀበለው ፡ አምልኮዬ ፡ ይኸው (፪x)