አዝ፦ በችግር ፡ ጓደኛ ፡ በመከራ
አብሮኝ ፡ የሚሰቃይ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በታናሽነቴ ፡ የማይንቀኝ
ዘመድ ፡ አግኝቻለሁ ፡ የሚወደኝ (፪x)
ኢየሱስ ፡ የሚባል ፡ ድንቅ ፡ መካር
የሰላም ፡ አለቃ ፡ ደግሞም ፡ ፍቅር
የሚባል ፡ ጓደኛ ፡ አግኝቻለሁ
እኔም ፡ በእርሱ ፡ ሰላም ፡ ረክቻለሁ
አዝ፦ በችግር ፡ ጓደኛ ፡ በመከራ
አብሮኝ ፡ የሚሰቃይ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በታናሽነቴ ፡ የማይንቀኝ
ዘመድ ፡ አግኝቻለሁ ፡ የሚወደኝ (፪x)
ችግሬን ፡ በሙሉ ፡ ወስዶት ፡ እርሱ
ደስታን ፡ ለእኔ ፡ ሰጠኝ ፡ ከመንፈሱ
ሃዘን ፡ ስወርድ ፡ አብሮኝ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ስደሰትም ፡ አብሮኝ ፡ በተራራ
አዝ፦ በችግር ፡ ጓደኛ ፡ በመከራ
አብሮኝ ፡ የሚሰቃይ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በታናሽነቴ ፡ የማይንቀኝ
ዘመድ ፡ አግኝቻለሁ ፡ የሚወደኝ (፪x)
ለነፍሱ ፡ ሳይሳሳ ፡ የሞተልኝ
እጅግ ፡ በጣም ፡ አድርጐ ፡ የሚወደኝ
አባት ፡ አግኝቻለሁ ፡ የማይተወኝ
እስከ ፡ ለዘለዓለም ፡ የሚመራኝ
አዝ፦ በችግር ፡ ጓደኛ ፡ በመከራ
አብሮኝ ፡ የሚሰቃይ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
በታናሽነቴ ፡ የማይንቀኝ
ዘመድ ፡ አግኝቻለሁ ፡ የሚወደኝ (፪x)