Wudu Balehuletaye (ውዱ ፡ ባለውለታዬ)

ሰላምህ ፡ በውስጤ ፡ እንደ ፡ ወንዝ ፡ ይፈሳል
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖልኛል
እኔም ፡ ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ልሰዋ
ባይስተካከልም ፡ ከውለታህ ፡ ጋራ

ሰላምህ ፡ በውስጤ ፡ እንደ ፡ ወንዝ ፡ ይፈሳል
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖልኛል
እኔም ፡ ምሥጋናዬን ፡ በፊትህ ፡ ልሰዋ
ባይስተካከልም ፡ ከውለታህ ፡ ጋራ (፪x)

አዝ፦ ውዱ ፡ ባለውለታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፪x)
ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ ፡ ማዳንህን ፡ አወራለሁ) ( (፬x)

እንተ ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ እኔም ፡ የአንተ ፡ ልጅ ፡ ነኝ
የሚያስደነግጠኝ ፡ ምንድነው ፡ ሚያሰጋኝ
ክንድህን ፡ ታምኘው ፡ በሰላም ፡ እኖራለሁ
ሁልጊዜ ፡ በዜማ ፡ ደስ ፡ አስኝሃለሁ (፪x)

አዝ፦ ውዱ ፡ ባለውለታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፪x)
ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ ፡ ማዳንህን ፡ አወራለሁ) ( (፬x)

최근에 들은 사람

0 코멘트
    댓글이 없습니다

:: / ::
::
/ ::

대기줄