Bamare Qine (ባማረ ፡ ቅኔ )

አዝ፦ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና
ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና
ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል
ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል


እኔስ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም ፡ ፍፁም ፡ አላፍርም ፡ ባዳነኝ ፡ ጌታ
አይቻለሁና ፡ በዐይኔ ፡ ያስጨነቀኝን ፡ ሲመታ
ነገር ፡ ባይሞላ ፡ ባይሳካ ፡ ኢየሱስ ፡ ምን ፡ ይሳነዋል
ከሞተው ፡ አንበሳ ፡ ሆድ ፡ ውስጥ ፡ ጣፋጭ ፡ ጣፋጭ ፡ ማር ፡ ያወጣል (፪x)

አዝ፦ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና
ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና
ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል
ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል


ለምን ፡ ልጐሳቆል ፡ ልዘን ፡ ለምንስ ፡ ልቆዝም ፡ በእንባ
ተዓምር ፡ ያስለመደኝ ፡ አምላክ ፡ መቼ ፡ ክንዱ ፡ ደከመና
በታሰርኩበት ፡ ወህኒ ፡ ውስጥ ፡ ሆ!፡ እያልኩኝ ፡ እዘምራለሁ
የጠላቶቼን ፡ ደጅ ፡ በእምነት ፡ በዝማሬ ፡ አፈርሳለሁ (፪x)

አዝ፦ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና
ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና
ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል
ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል


ውድቀቴን ፡ ጠላቴ ፡ ሰምቶ ፡ ከበሮ ፡ ተይዞ ፡ ሲጨፈር
አምላኩ ፡ ጥሎታል ፡ ዛሬስ ፡ ተብሎ ፡ አዋጅ ፡ ሲነገር
ሰው ፡ የማይጥል ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ ኃያል ፡ ክንዱን ፡ ሲዘረጋ
ጠላቶቼ ፡ ሁሉ ፡ አለቁ ፡ በአንዲት ፡ የአህያ ፡ መንጋጋ (፪x)

አዝ፦ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና
ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና
ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል
ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል


ሰላሙን ፡ ሞልቶ ፡ አባቴ ፡ በመስቀሉ ፡ ስራ ፡ አሳረፈኝ
ወደ ፡ ክብሩ ፡ ልጁም ፡ መንግሥት ፡ በታላቅ ፡ ፍቅሩ ፡ አፈለሰኝ
ልጁን ፡ ለእኔ ፡ የሰጠ ፡ አምላክ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ምን ፡ ይሳነዋል
ባዶ ፡ ሸለቆዬ ፡ ሞልቶ ፡ ተርፎ ፡ ለአገር ፡ ሁሉ ፡ ይፈሳል (፪x)

አዝ፦ ባማረ ፡ ቅኔ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና
ቃሉን ፡ የሚያደርግ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነውና
ደመናም ፡ ባላይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል
ሰው ፡ የማይችለው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይቻላል

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue