Albash Adegeg (አልባሽ ፡ አርገኝ)

አዝ፦ የወንድሞቼ ፡ የእህቶቼን
እራቁት ፡ አልባሽ ፡ አርገኝ ፡ እግዚአብሔር
የካም ፡ መንፈስ ፡ ይራቅ ፡ ከእኔ
እልባሽ ፡ አርገኝ ፡ ለወገኔ (፪x)

ኖህን ፡ ልጁ ፡ አዋረደው
አንድ ፡ ቀን ፡ ድንገት ፡ ሰክሮ ፡ ቢያየው [1]
ምን ፡ አለበት ፡ ልብስ ፡ ቢያለብሰው
ይህ ፡ ቀን ፡ አልፎ ፡ እኮ ፡ ይሆናል ፡ ሰው

አዝ፦ የወንድሞቼን ፡ የእህቶቼን
ገመና ፡ ሸፋኝ ፡ አርገኝ ፡ እግዚአብሔር
የካም ፡ መንፈስ ፡ ይራቅ ፡ ከእኔ
አልባሽ ፡ አርገኝ ፡ ለወገኔ

ብዙ ፡ . (1) . ፡ ለብሰዋል
የንስሃ ፡ ጊዜ ፡ እጥተዋል
ራቁትነትን ፡ አልባሽ ፡ ጠፍቶ
ቀረ ፡ የትም ፡ ህዝብህ ፡ ወጥቶ

አዝ፦ የወንድሞቼን ፡ የእህቶቼን
እራቁት ፡ አልባሽ ፡ አርገኝ ፡ እግዚአብሔር
የካም ፡ መንፈስ ፡ ይራቅ ፡ ከእኔ
አልባሽ ፡ አርገኝ ፡ ለወገኔ

ድካም ፡ መግለጥ ፡ የወንድምን
መሰብሰብ ፡ ነው ፡ ራስ ፡ መርገምን
አይጠቅመንም ፡ ለእኔም ፡ ለእርሱም
ይልቅ ፡ ይበጃል ፡ ልብስ ፡ ማልበሱ

አዝ፦ የወንድሞቼን ፡ የእህቶቼን
ገመና ፡ ሸፋኝ ፡ አርገኝ ፡ እግዚአብሔር
የካም ፡ መንፈስ ፡ ይራቅ ፡ ከእኔ
አልባሽ ፡ አርገኝ ፡ ለወገኔ

ለወንድሜ ፡ ጥቃት ፡ ደራሽ
እራቁትነቱን ፡ አልባሽ
የደከመን ፡ ማበረታ
ምርጫዬ ፡ ነው ፡ ልሁን ፡ ጌታ

አዝ፦ የወንድሞቼን ፡ የእህቶቼን
ገመና ፡ ሸፋኝ ፡ አርገኝ ፡ እግዚአብሔር
የካም ፡ መንፈስ ፡ ይራቅ ፡ ከእኔ
አልባሽ ፡ አርገኝ ፡ ለወገኔ

የአባታቸውን ፡ ሀፍረት ፡ ማየት
አልውደዱም ፡ ሴምና ፡ ያፌት
ሸማ ፡ አምጥተው ፡ አለበሱት
ቀን ፡ መጣለት ፡ በረታ ፡ አሱም [2]

አዝ፦ የወንድሞቼን ፡ የእህቶቼን
ድካም ፡ አጋዥ ፡ አርገኝ ፡ እግዚአብሔር
የካም ፡ መንፈስ ፡ ይራቅ ፡ ከእኔ
አልባሽ ፡ አርገኝ ፡ ለወገኔ (፫x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue