Emenet Ketateqe (እምነት ፡ ከታጠቀ)

አዝ፦ እምነት ፡ ከታጠቀ ፡ አምላኩን ፡ ከጠራ
አማኝ ፡ ድል ፡ አይሆንም ፡ በእሳት ፡ በመከራ
እምነት ፡ የሁሉም ፡ መሠረት (፪x)

ተጠራጣሪ ፡ ሰው ፡ ጌታን ፡ ያኮሰሰ
በጠላት ፡ ተማርኮ ፡ ተረቶ ፡ አለቀሰ (፪x)
በእምነት ፡ ግን ፡ የገባ ፡ የጠላቱን ፡ መንደር
አሸንፎ ፡ ሳቀ ፡ የጌታ ፡ ወታደር

አዝ፦ እምነት ፡ ከታጠቀ ፡ አምላኩን ፡ ከጠራ
አማኝ ፡ ድል ፡ አይሆንም ፡ በእሳት ፡ በመከራ
እምነት ፡ የሁሉም ፡ መሠረት (፪x)

ታምኖ ፡ የወጣ ፡ ሰው ፡ የእምነት ፡ ችቦ ፡ አንድዶ
ጠላቱን ፡ አጠፋ ፡ ኢያርኮን ፡ ንዶ (፪x)
አምላኩን ፡ ፈትኖ ፡ እምነት ፡ ከታጠቀ
በተረከዙ ፡ ጫፍ ፡ ባህር ፡ አደረቀ

አዝ፦ እምነት ፡ ከታጠቀ ፡ አምላኩን ፡ ከጠራ
አማኝ ፡ ድል ፡ አይሆንም ፡ በእሳት ፡ በመከራ
እምነት ፡ የሁሉም ፡ መሠረት (፪x)

በፊቱ ፡ ቢጋረድ ፡ ተስፋ ፡ ሲያስቆርጠው
የእምነት ፡ ዘንግ ፡ አንስቶ ፡ ባሕሩን ፡ ከፈለው (፪x)
በድል ፡ ተሻገረ ፡ የእምነት ፡ ካባ ፡ አጥልቆ
ዳግም ፡ ላይደርስበት ፡ ከጠላቱ ፡ ርቆ

አዝ፦ እምነት ፡ ከታጠቀ ፡ አምላኩን ፡ ከጠራ
አማኝ ፡ ድል ፡ አይሆንም ፡ በእሳት ፡ በመከራ
እምነት ፡ የሁሉም ፡ መሠረት (፪x)

최근에 들은 사람

0 코멘트
    댓글이 없습니다

:: / ::
::
/ ::

대기줄