ለክብሩ ፡ ዘምሩ

አዝ፦ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ውዳሴና ፡ ዕልልታ
ይገባሃል ፡ አንተ ፡ የእኛ ፡ ጌታ
እግዚአብሔርን ፡ የምትወዱ ፡ ኦሆ ፡ የምትፈሩ ፡ አሃ
ተነሱ ፡ ለክብሩ ፡ ዘምሩ (፪x)

ሠማያዊ ፡ ሚስጢር ፡ የገለጸላችሁ
ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ መጥቶ ፡ ያወጣችሁ
ይህን ፡ እግዚአብሔርን ፡ እስኪ ፡ እናመስግነው
በዝማሬ ፡ ዕልልታ ፡ ክበር ፡ እንበለው

አዝ፦ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ውዳሴና ፡ ዕልልታ
ይገባሃል ፡ አንተ ፡ የእኛ ፡ ጌታ
እግዚአብሔርን ፡ የምትወዱ ፡ ኦሆ ፡ የምትፈሩ ፡ አሃ
ተነሱ ፡ ለክብሩ ፡ ዘምሩ (፪x)

የምድር ፡ ሁሉ ፡ ደስታ ፡ የፅዮን ፡ ተራራ
እግዚአብሔር ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ክብሩ ፡ የሚያስፈራ
እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ ከቶ ፡ ስላላየን
ለታላቁ ፡ ጌታ ፡ እንሰግድለታለን

አዝ፦ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ውዳሴና ፡ ዕልልታ
ይገባሃል ፡ አንተ ፡ የእኛ ፡ ጌታ
እግዚአብሔርን ፡ የምትወዱ ፡ ኦሆ ፡ የምትፈሩ ፡ አሃ
ተነሱ ፡ ለክብሩ ፡ ዘምሩ (፪x)

አዲስን ፡ ዝማሬ ፡ ለእርሱ ፡ ዘምሩ
ታላቅነቱንም ፡ ግርማውንም ፡ አውሩ
ክብሩን ፡ ለአሕዛብ ፡ እንናገራለን
ተዓምራቱን ፡ ደግሞ ፡ እኛ ፡ እናወራለን

አዝ፦ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ውዳሴና ፡ ዕልልታ
ይገባሃል ፡ አንተ ፡ የእኛ ፡ ጌታ
እግዚአብሔርን ፡ የምትወዱ ፡ ኦሆ ፡ የምትፈሩ ፡ አሃ
ተነሱ ፡ ለክብሩ ፡ ዘምሩ (፪x)

የእርሱን ፡ በጐነት ፡ መልካምነቱን
ማለዳ ፡ ማለዳ ፡ ምሕረቱን ፡ ካየን
በፀጋው ፡ በፍቅሩ ፡ ጠብቆ ፡ ላቆመን
ቆመን ፡ ከነፍሳችን ፡ ምሥጋና ፡ እንሰጣለን

አዝ፦ ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ውዳሴና ፡ ዕልልታ
ይገባሃል ፡ አንተ ፡ የእኛ ፡ ጌታ
እግዚአብሔርን ፡ የምትወዱ ፡ ኦሆ ፡ የምትፈሩ ፡ አሃ
ተነሱ ፡ ለክብሩ ፡ ዘምሩ (፪x)

ተነሱ ፡ ለክብሩ ፡ ዘምሩ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue