Dil Lemadreg Weta (ድል ፡ ለማድረግ ፡ ወጣ)

የፈርዖን ፡ ገንዘብ ፡ ያልማረከው ፡ ጀግና
ዓይኑ ፡ ያልደከመ ፡ ያላለቀ ፡ ገና
ድል ፡ ለማድረግ ፡ ወጣ ፡ በጦርነት ፡ ሲቃ
በጀርባው ፡ አንግቦ ፡ የአምላኩን ፡ ጦር ፡ ዕቃ (፪x)

የወይኒው ፡ አስራት ፡ የግርፋት ፡ ብዛት
አልቻለው ፡ ሊያበርደው ፡ የፍቅሩን ፡ ትኩሳት
ፎከረ ፡ ያ ፡ ጐበዝ ፡ ሊጥል ፡ ሊገረስስ
ጠምዶ ፡ በቀኝ ፡ እጁ ፡ የቃሉን ፡ መትረየስ (፪x)

የልብ ፡ ዓይኑ ፡ ፈጦ ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ እያየ
የጠላትን ፡ ምሽግ ፡ ሰፈሩን ፡ አጋዬ
የአርያም ፡ እሳት ፡ በኃይል ፡ ጐብኝቶታል
እባቡና ፡ ጊንጡን ፡ ከእግሩ ፡ ስር ፡ ረግጦታል (፪x)

በድካም ፡ በረታ ፡ ጅማቱ ፡ ጠንክሯል
አንገብግቦት ፡ ፍቅሩ ፡ ወኔው ፡ ተቀስቅሷል
በጀርባው ፡ መተልተል ፡ ጌታን ፡ አከበረ
የሞትንም ፡ ባሕር ፡ በእምነት ፡ ተሻገረ (፪x)

Đã nghe gần đây bởi

0 bình luận
    Không tìm thấy bình luận

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Xếp hàng