• 58
  • 3
  • 0
  • 1
  • 0

Meserete Kirstos Choir- Enakebrehalen ( እናከብርሃለን)

አዝ፦ እናከብርሃለን ፡ እናነግስሃለን
ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ማዳንህም ፡ ለዘላለም
ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ተዓምር
ይገባሃል ፡ ዛሬም ፡ ክበር (፪x)

በኃጢአት ፡ ወድቀን ፡ ወንጌል ፡ ሰበክልን
አሮጌውን ፡ ሕይወት ፡ በአዲስ ፡ ለወጥክልን
ቀንበራችን ፡ ሰብረህ ፡ ነጻ ፡ አወጣኸን
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከብረህ ፡ አከበርከን

አዝ፦ እናከብርሃለን ፡ እናነግስሃለን
ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ማዳንህም ፡ ለዘላለም
ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ተዓምር
ይገባሃል ፡ ዛሬም ፡ ክበር

ስጦታ ፡ ስትሰጥ ፡ እጆችህ ፡ መሉዎች
በመንፈስ ፡ በፀጋ ፡ በክብር ፡ ታላቆች
በአደባባዮችህ ፡ ሰንቆም ፡ በምሥጋና
ከዓመታት ፡ መካከል ፡ ክበር ፡ እንደገና

አዝ፦ እናከብርሃለን ፡ እናነግስሃለን
ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ማዳንህም ፡ ለዘላለም
ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ተዓምር
ይገባሃል ፡ ዛሬም ፡ ክበር

በሞገስ ፡ በክብር ፡ በግርማ ፡ ያለኸው
ልዑል ፡ ዙፋንህን ፡ ማንም ፡ የማይሽረው
ሥጋና ፡ ነፍሳችን ፡ መንፈሳችን ፡ ሁሉ
በእውነትና ፡ በመንፈስ ፡ ለአንተ ፡ ይገዛሉ

አዝ፦ እናከብርሃለን ፡ እናነግስሃለን
ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ማዳንህም ፡ ለዘላለም
ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ተዓምር
ይገባሃል ፡ ዛሬም ፡ ክበር

ዛሬም ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ሰላምን ፡ ሰጥተኽን
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በቀኝ ፡ አስቀመጥከን
በዚህ ፡ ሳንወሰን ፡ ጽዮን ፡ እንገባለን
ለዘለዓለም ፡ በፍትህ ፡ እንዘምራለን

አዝ፦ እናከብርሃለን ፡ እናነግስሃለን
ውለታህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ
ማዳንህም ፡ ለዘላለም
ሥራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ተዓምር
ይገባሃል ፡ ዛሬም ፡ ክበር (፪x)

সম্প্রতি দ্বারা শোনা

0 মন্তব্য
    কোন মন্তব্য পাওয়া যায়নি

:: / ::
::
/ ::

কিউ