Maranatha (ማራናታ)

"ልባችሁ ፡ አይታወክ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እመኑ ፡
በእኔም ፡ ደግሞ ፡ እመኑ ፤
በአባቴ ፡ ቤት ፡ ብዙ ፡ መኖሪያ ፡ አለ ፤
እንዲህስ ፡ ባይሆን ፡ ባልኋቹ ፡ ነበር ፡፡
ስፍራ ፡ አዘጋችላቹህ ፡ ዘንድ ፡ እሄዳለሁና ፤
ሄጄም ፡ ስፍራ ፡ ባዘጋጅላችሁ ፡ እኔ ፡
ባለሁበት ፡ እናንተ ፡ ደግሞ ፡ እንድትሆኑ ፡
ሁለተኛ ፡ እመጣለሁ ፡ ወደ ፡ እኔም ፡ እወስዳችኋለሁ"

ያስጨነቀንን ፡ ሁሉ ፡ ደግመን ፡ ልናስበው
እንባችንን ፡ ሊያብስ ፡ ሃዘንን ፡ ሊያርቀው
ይህንን ፡ ፈራሽ ፡ ሥጋ ፡ በክብር ፡ ሊለውጠው
ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ እግዚአብሔር ፡ ቃሉን ፡ ሊፈጽመው

ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል
ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ ይመጣል
ይመጣል ፡ በክብር ፡ ይመጣል (፪x)

ጠላት ፡ ጦር ፡ አውጥቶ ፡ ቢያጥር ፡ ዙሪያችንን
ኑሮው ፡ ትግል ፡ ሆኖ ፡ ቢያዝል ፡ ቢያደክመን
የጠበቅነው ፡ ኢየሱስ ፡ በክብር ፡ ሲመጣልን
እኛም ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ አብረን ፡ እንከብራለን

ይመጣል ፡ ጌታ ፡ ይመጣል
ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ ይመጣል
ይመጣል ፡ በክብር ፡ ይመጣል (፪x)

እግዚአብሔር ፡ መለከት ፡ ከሠማይ ፡ ይወርዳል
የወጉትም ፡ ሁሉ ፡ በዓይናቸው ፡ ያዩታል
በሙታን ፡ ሕያው ፡ ላይ ፡ ሊፈርድ ፡ ይገለጣል
የጌታ ፡ ምጻቱ ፡ ጊዜያቱ ፡ ተቃርቧል

ማራናታ ፡ ማራናታ ፡ ማራናታ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

ቃሉን ፡ የሰጠን ፡ የታመነ ፡ ነው
በክብር ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ የተቀመጠው
ወላጅ ፡ እንደሌለው ፡ ከቶ ፡ ላይተወን
ይመጣል ፡ ኢየሱስ ፡ ሃሌሉያ ፡ እኛን ፡ ሊወስደን (፪x)

ማራናታ ፡ ማራናታ ፡ ማራናታ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue