Yelibe Amlak Hoy (የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ)

እግዚአብሔርን ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ ያደረኩት
ታማኝነቱን ፡ አይቼ ፡ እጄን ፡ ልቤን ፡ የሰጠሁት
ያለ ፡ አዋቂዎች ፡ ልቦና ፡ በሰዎች ፡ ተስፋ ፡ ያደርጋል
ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ድህንነትን ፡ ያዘጋጃል

አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማፀን ፡ አይተኸኝ
እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ
በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ

የተማሰው ፡ ጉድጓድ ፡ አፉን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አልዘጋም
ጉልበቴ ፡ ባለቀ ፡ ጊዜ ፡ ለብቻዬ ፡ አልተውከኝም
ስለ ፡ ትንሿ ፡ እምነቴ ፡ ከባለጋራ ፡ ተሟግተህ
የድል ፡ አምባ ፡ አስረገጥከኝ ፡ ውጊያውን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽመህ

አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማፀን ፡ አይተኸኝ
እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ
በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ

ምሥጋናዬን ፡ እያዜምኩኝ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
በከንቱ ፡ በሚጠሉኝ ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ አጐናጽፈኸኛል
ዓለም ፡ ብትሰርዘኝም ፡ የሕይወት ፡ መዝገብ ፡ አውቆኛል
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ድረስ ፡ ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ ይጸናል

አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማፀን ፡ አይተኸኝ
እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ
በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ
የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue