Yeseralignin Dink (የሰራልኝን ፡ ድንቅ)

አዝ፦ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ

በእለት እርምጃዬ ፡ እግሬ ፡ ኢየሱስ ፡ ቀድሞ
ምህረቱን ፡ አብዝቶ ፡ ተዓምራቱን ፡ ደግሞ
አሳየኝ ፡ አምላኬ ፡ የከበረ ፡ ነገር
እንደዚህ ፡ ሊመራኝ ፡ ወደ ፡ ፃድቃን ፡ አገር (፪x)

አዝ፦ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ

በቀኝ ፡ በግራዬ ፡ አድፍጦ ፡ አድብቶ
መልካም ፡ መሰል ፡ አጥፊ ፡ ወጥመዱን ፡ ዘርግቶ
ጌታ ፡ ግን ፡ ሲያድነኝ ፡ በጦር ፡ ተደራጅቶ
ዲያብሎስ ፡ ሊያጠቃኝ ፡ ነበር ፡ ተሰናድቶ (፪x)

አዝ፦ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ

እርሱ ፡ ቅጥር ፡ ሲቀጥር ፡ በእምላኬ ፡ እየዘለልኩ
ወጥመድ ፡ ሲዘረጋ ፡ እኔም ፡ እያመለጥኩ
በእኔ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ በጌታ ፡ እየታመንኩ
ሩጫ ፡ ቀጥላለሁ ፡ ሁሉን ፡ እያሸነፍኩ (፪x)

አዝ፦ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ

በዘለዓለም ፡ መድህን ፡ ከጥልቁ ፡ ወጥቼ
ከአባት ፡ ከእናት ፡ ዘመድ ፡ የሚበልጥ ፡ አግኝቼ
በአህዛብ ፡ መሃከል ፡ ለርሱ ፡ ዘምራለሁ
የከበረ ፡ ሥሙን ፡ አመሰግናለሁ (፪x)

አዝ፦ የሰራልኝን ፡ ድንቅ ፡ ታሪኩን ፡ ላውጋችሁ
ሰዎች ፡ እስኪ ፡ ስሙ ፡ ትምህርት ፡ ይሁናችሁ
በጌታ ፡ ይታመን ፡ ይጽናና ፡ ልባችሁ

최근에 들은 사람

0 코멘트
    댓글이 없습니다

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

대기줄