Tesfayie (ተስፋዬ)

ተስፋዬ ፡ ነህ ፡ አንተ
ማረፊያዬ ፡ አንተ
መታመንስ ፡ አንተ ፡ ኦ
መመኪያ ፡ ነህ ፡ አንተ
መመኪያዬ (፰x)

ተስፋዬ ፡ አንተው ፡ ነህ
ንጉሤ ፡ አንተው ፡ ነህ
አምላኬ ፡ አንተው ፡ ነህ
ወዳጄ ፡ አንተው ፡ ነህ
የሚሳንህ ፡ የለም ፡ ንገሥ
የሚያቅትህ ፡ የለም ፡ ንገሥ
የሚሳንህ ፡ የለም ፡ ንገሥ
የሚያቅትህ ፡ የለም ፡ ንገሥ (፪x)

ከሸለቆ ፡ ወጣሁ ፡ ተራራ ፡ ላይ ፡ ቆምኩኝ
ከረግረግ ፡ ውስጥ ፡ ወጣሁ ፡ እጄንም ፡ ተያዝኩኝ
የጠላቴን ፡ አንገት ፡ ያስረገጠኝ ፡ ጌታ
ይክበር ፡ ይንገሥልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ

ተስፋዬ ፡ ነህ ፡ አንተ
ማረፊያዬ ፡ አንተ
መታመንስ ፡ አንተ ፡ ኦ
መመኪያ ፡ ነህ ፡ አንተ
መመኪያዬ (፰x)

በበረሃ ፡ ጋሻ ፡ ለተጠማ ፡ እርካታ
ስትሆን ፡ አየሁህ ፡ የእርሱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ጀርባህን ፡ ለደካማ ፡ ለበረታው ፡ ፊትህን
ሰጥተህ ፡ አታደላም ፡ ሥምህ ፡ ብሩክ ፡ ይሁን (፭x)

ለታላቅነትህ ፡ እቀኛለሁ
ለጌትነትህም ፡ እሰግዳለሁ (፫x)
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x)

የምስኪኑን ፡ ጥሪ ፡ ጩኸት ፡ ትሰማለህ
በባዕድ ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ አባት ፡ ትሆናለህ
የተገፋን ፡ ማንሳት ፡ ማክበር ፡ ልማድህ ፡ ነው
በሠማይ ፡ በምድር ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው (፬x)

ለታላቅነትህ ፡ እቀኛለሁ
ለጌትነትህም ፡ እሰግዳለሁ ፫x)
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x)

ተስፋዬ ፡ ነህ ፡ አንተ
ማረፊያዬ ፡ አንተ
መታመንስ ፡ አንተ ፡ ኦ
መመኪያ ፡ ነህ ፡ አንተ
መመኪያዬ (፰x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue