Egziabhieren Bemetemamen (እግዚአብሔርን ፡ በመተማመን)

ኧረ ፡ ስንቱ ፡ በአንተ ፡ ታለፈ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ታለፈ (፪x)

እግዚአብሔርን ፡ በመተማመን ፡ የሚጠባበቁ ፡ ሁሉ
ኃይላቸውን ፡ ያድሳሉ
እንደ ፡ ንስር ፡ በክንፍ ፡ ይወጣሉ

መስሎት ፡ ነበር ፡ ጠላቴ ፡ ደክሜ ፡ የምቀር
እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ አበረታኝ ፡ ሆነልኝ ፡ ግርማ ፡ ሞገስ
ዛሬ ፡ ይኸው ፡ ዘምራለሁ ፡ ድካሜን ፡ ረስቻለሁ
ሥምህን ፡ አከብራለሁ ፡ ንገሥ ፡ እልሃለሁ (፪x)

አልደከምኩም ፡ አልታከትኩም ፡ ጌታ ፡ ሆኖኝ ፡ ኃይሌ
ዘለዓለም ፡ አመልከዋለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
በደስታ ፡ በዕልልታ ፡ በአክብሮት ፡ ደግሞም ፡ በሆታ
ሥምህን ፡ አከብራልሁ ፡ ንገሥ ፡ እልሃለሁ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue