እኔን ፡ አልረሳኝም

ይህ ፡ እግዚአብሔር ፡ በእውነትም
የተናገርውን ፡ ይፈጽማል (፪x)

አዝ፦ ማንን ፡ ይረሳል ፡ ጌታ ፡ ማንን ፡ ይረሳል
ማንን ፡ ይረሳል ፡ ኢየሱስ ፡ ማንን ፡ ይረሳል
እኔን ፡ አልረሳኝም ፡ ጌታዬ ፡ አስቦኛል
እንደተናተረው ፡ በእርግጥ ፡ አርጐልኛል (፪x)

ጠላቴ ፡ አሳዶ ፡ አድክሞኝ ፡ ሊይዘኝ
ሰይፍ ፡ ሲምዝብኝ ፡ ጨክኖ ፡ ሊያጠፋኝ
ንፋሱን ፡ አንፍሶ ፡ ባሕሩን ፡ ከደነው
በኃይለኛው ፡ ክንዱ ፡ ጠላቴን ፡ በተነው

አዝ፦ ማንን ፡ ይረሳል ፡ ጌታ ፡ ማንን ፡ ይረሳል
ማንን ፡ ይረሳል ፡ ኢየሱስ ፡ ማንን ፡ ይረሳል
እኔን ፡ አልረሳኝም ፡ ጌታዬ ፡ አስቦኛል
እንደተናተረው ፡ በእርግጥ ፡ አርጐልኛል (፪x)

ተስፋ ፡ ትቆርጦበት ፡ መቃብር ፡ ተዘግቶ
የወዳጆቹም ፡ ልብ ፡ በሃዘን ፡ ተሞልቶ
በተዓምር ፡ ይናል ፡ ብሎ ፡ ተናገረ
በአላዛር ፡ ትንሳኤ ፡ ሥሙን ፡ አከበረ

አዝ፦ ማንን ፡ ይረሳል ፡ ጌታ ፡ ማንን ፡ ይረሳል
ማንን ፡ ይረሳል ፡ ኢየሱስ ፡ ማንን ፡ ይረሳል
እኔን ፡ አልረሳኝም ፡ ጌታዬ ፡ አስቦኛል
እንደተናተረው ፡ በእርግጥ ፡ አርጐልኛል (፪x)

አቤት ፡ እግዚአብሔር ፡ እንደምን ፡ ድንቅ ፡ ነህ
ዛሬም ፡ በእኔ ፡ ሕይወት ፡ ቃልህን ፡ ጠብቀህ
የፍቅርህ ፡ ዓይንህ ፡ አርፎ ፡ በድካሜ ፡ ላይ
በፀጋህ ፡ በርትቼ ፡ ቆሜ ፡ የለም ፡ ዎይ

አዝ፦ ማንን ፡ ይረሳል ፡ ጌታ ፡ ማንን ፡ ይረሳል
ማንን ፡ ይረሳል ፡ ኢየሱስ ፡ ማንን ፡ ይረሳል
እኔን ፡ አልረሳኝም ፡ ጌታዬ ፡ አስቦኛል
እንደተናተረው ፡ በእርግጥ ፡ አርጐልኛል (፪x)

ይህ ፡ እግዚአብሔር ፡ በእውነትም
የተናገርውን ፡ ይፈጽማል (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue