Kesemahut Belay (ከሰማሁት ፡ በላይ)

አምላክነትህን ፡ ታላቅነትህ ፡ ጌትነትህ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት (፪x)

አምላኬ (፫x) ፡ እያልኩኝ
በፊትህ ፡ ብሰግድ ፡ ያለኝን ፡ ባስቀምጥ
ቃላት ፡ አላገኝም ፡ ክብርህን ፡ የሚገልጥ (፪x)

አዝ፦ መልካምነትህ ፡ አባትነትህ ፡ ደግነትህ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት (፪x)

ምህረት ፡ ቸርነትህ ፡ ተከትለውኛል
በፀጋ ፡ ላይ ፡ ፀጋ ፡ ፍቅርህ ፡ ደግፎኛል
መልካም ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ በስጦታህ ፡ አትጸጸት
ቆጥሬ ፡ አልጨርስም ፡ ጌታ ፡ የአንተን ፡ ደግነት (፪x)

አዝ፦ መልካምነትህ ፡ አባትነትህ ፡ ደግነትህ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት (፪x)

በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ የማውቀው ፡ እውነቱ
ቀዝቅዞ ፡ አያውቅም ፡ መውደድህ ፡ ግለቱ
የፍቅርህ ፡ ስፋቱ ፡ ልክ ፡ የለው ፡ ጥልቀቱ
በመስቀል ፡ ተገልጧል ፡ አምሳያ ፡ ማጣቱ

አዝ፦ አምላክነትህ ፡ ታማኝነትህ ፡ ወዳጅነትህ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ከገመትኩት (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue