እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ

ከአፌ ፡ የወጣው ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ሳያፈራ
ከቶ ፡ አይመለስም ፡ ሥራውን ፡ ሳይሰራ [1]
ብሎ ፡ የተናገረው ፡ ለሥሙ ፡ የሚቀና
ገና ፡ አሁን ፡ እናያለን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ (፪x)

እንደነቃልን ፡ እንደነቃልን
እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ ፡ በዓይናችን ፡ እያየን (፪x)

በዓይናችን ፡ እያየን (፬x)

ይህ ፡ እንዴት ፡ ይሆናል ፡ ማንስ ፡ ያውቅበታል
ያስ ፡ እንደምን ፡ ሆኖ ፡ ወደዚህ ፡ ይደርሳል
በመንፈሱ ፡ እንጂ ፡ በኃይል ፡ የማይሆነው
የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ ሁሌም ፡ ፍጻሜ ፡ አለው (፪x)

እንደነቃልን ፡ እንደነቃልን
እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ ፡ በዓይናችን ፡ እያየን (፪x)

በዓይናችን ፡ እያየን (፬x)

እግዚአብሔር ፡ የሚያስመካ
የሚያስደንቅ ፡ የሚያኮራ
ሥራው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ሲሰራ
ሥራው ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ሲሰራ (፪x)

የሚታመን ፡ በአንተ ፡ ይታመን
የሚመካ ፡ በአንተ ፡ ይመካ
የሚደገፍ ፡ በአንተ ፡ ይደገፍ
የሚኮራ ፡ በአንተ ፡ ይኩራ

እኛስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ ይለናል ፡ ይለናል (፪x)
በአንተ ፡ መደገፉ ፡ ያስመካናል (፪x)
የአንተ ፡ መሆናችን ፡ ያስመካናል (፪x)

እኛስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ ይለናል ፡ ይለናል (፪x)
በአንተ ፡ መደገፉ ፡ ያስመካናል (፪x)
በአንተ ፡ መታየቱ ፡ ያስመካናል (፪x)
በአንተ ፡ መደገፉ ፡ ያስመካናል (፪x)
በአንተ ፡ መታየቱ ፡ ያስመካናል (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue