• 127
  • 0
  • 0
  • 0
  • 0

ህልሜ (Helmie)

ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ሃሳቤን ፡ ጥላለሁ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ጭንቀቴን ፡ ረሳለሁ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ሰላሜ ፡ ሙሉ ፡ ነው
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ደስታዬ ፡ ፍፁም ፡ ነው

ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ሃዘኔን ፡ ተዋለሁ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ጉድለቴን ፡ ረሳለሁ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ለሊቱም ፡ ይነጋል
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ባዶዬ ፡ ይሞላል

አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ
ህልሜ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ኦሆሆ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ
ውዴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ኦሆሆ
ውዴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ

ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሳየው ፡ ተራራው ፡ ይናዳል
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሳየው ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላል
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ እኔ ፡ አይላለሁ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ጠላቴን ፡ ጥላለሁ

ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ድካሜን ፡ ረሳለሁ
ክንድህን ፡ ተደግፌ ፡ በአንተ ፡ እመካለሁ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ስሆን ፡ ከቶ ፡ የለኝ ፡ ከልካይ
የአባትነት ፡ ፍቅርህ ፡ ልጅነቴ ፡ ገብቶኝ

አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ
ህልሜ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ኦሆሆ
ጌታ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ
ውዴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ኦሆሆ
ውዴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ የነፍስ ፡ ጩኸቷ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ መሆን ፡ ሁልጊዜ ፡ ናፍቆቷ
ፊትህን ፡ እያየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ላመልክህ
ክብርህን ፡ እያየሁ ፡ ወድቄ ፡ ላደንቅህ

አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ
ህልሜ ፡ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ
ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ፡ አሃሃ
ዙፋንህን ፡ ማየቴ
ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ፡ ኦሆሆ
ክብርህን ፡ ማየቴ

ዙፋንህ ፡ ሥር ፡ ሆኜ ፡ እኔም ፡ አሰግዳለሁ
ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ እላለሁ
ባልተሰማ ፡ ቅኔ ፡ ያኔ ፡ አቀኛለሁ
ከመላዕቶችህ ፡ ጋር ፡ አብሬ ፡ አሰግዳለሁ

አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ
ህልሜ ፡ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ
ክብርህን ፡ ማየቴ ፡ ኦሆሆ
ክብርህን ፡ ማየቴ
ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ፡ አሃሃ
ዙፋንህን ፡ ማየቴ

የሚጠፋው ፡ አልፎ ፡ የሚጠፋውን ፡ ስለብስ
እሩጫዬ ፡ አልቆ ፡ ዘለዓለሜ ፡ ስደርስ
ያኔ ፡ የፍቅር ፡ ፊትህን ፡ ፊት ፡ ለፊቴ ፡ ሳየው
በምን ፡ ቋንቋ ፡ ይሆን ፡ መውደዴን ፡ ምገልጸው

አዝ፦ ህልሜ ፣ ህልሜ
ህልሜ ፡ ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ
ክብርህን ፡ ማየቴ ፡ ኦሆሆ
ክብርህን ፡ ማየቴ
ውብ ፡ ፊትህን ፡ ማየቴ ፡ ኦሆሆ
ክብርህን ፡ ማየቴ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue