Meserete Kirstos Choir- Endante Manem Yelem (እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም)

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ማን
እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ መድኃኒት ፡ ለዓለም
ኢየሱስ ፡ ካለ ፡ አንተ ፡ የለም (፪x)

መሄጃ ፡ ለጠፋው ፡ ግራ ፡ ለገባው ፡ ሰው
የኃጢአት ፡ ቀንበር ፡ ከብዶት ፡ ሸክም ፡ ለተጫነው
ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጣና ፡ አሳርፈዋለሁ
የሚል ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማነው

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ማን
እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ መድኃኒት ፡ ለዓለም
ኢየሱስ ፡ ካለ ፡ አንተ ፡ የለም

ልከፍለው ፡ የማልቻል ፡ ዕዳ ፡ ተሸክሜ
በዘላለም ፡ ደዌ ፡ በኃጢአት ፡ ታምሜ
በጐልጐታ ፡ መስቀል ፡ ዕዳዬን ፡ ከፍለሃል
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ወዳጅ ፡ ኧረ ፡ የት ፡ ይገኛል

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ማን
እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ መድኃኒት ፡ ለዓለም
ኢየሱስ ፡ ካለ ፡ አንተ ፡ የለም

ኃጢአተኛ ፡ ብሎ ፡ ሰው ፡ ሲፈርድባት
በድንጋይ ፡ ውግራት ፡ ሞት ፡ ተወስኖባት
አንተ ፡ ግን ፡ በምህረት ፡ ፍርዷን ፡ ለወጥከና
ነጻ ፡ ሰው ፡ አደረካት ፡ ለሥምህ ፡ መሥጋና

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ማን
እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ መድኃኒት ፡ ለዓለም
ኢየሱስ ፡ ካለ ፡ አንተ ፡ የለም

ለብዙ ፡ ዘመናት ፡ ከአልጋ ፡ ተቆራኝቶ
ወደ ፡ መጠመቂያው ፡ የሚያስገባው ፡ አጥቶ
ረዳትና ፡ አጋዥ ፡ ወገን ፡ ለሌለው ፡ ሰው
አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ የደረስከው

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ማን
እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ መድኃኒት ፡ ለዓለም
ኢየሱስ ፡ ካለ ፡ አንተ ፡ የለም

ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ሕዝቦችን ፡ ልትዋጅ
የአምላካችን ፡ መንግሥት ፡ ቃላት ፡ ልታዘጋጅ
ስለ ፡ ኃጢአታችን ፡ እንደ ፡ በግ ፡ ታርደሃል
በረከት ፡ ምሥጋና ፡ ክብርም ፡ ይገባሃል

አዝ፦ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እንዳንተ ፡ ማን
እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ መድኃኒት ፡ ለዓለም
ኢየሱስ ፡ ካለ ፡ አንተ ፡ የለም (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue