Dagmawi Tilahun--Yedesta Menfes (የደስታ ፡ መንፈስ)

እኔስ ፡ በአምላኬ ፡ በጌቶች ፡ ጌታ
ይህ ፡ ነው ፡ አይባልም ፡ ያለኝ ፡ ደስታ
ደመና ፡ ሳይኖር ፡ በአካባቢዬ
ግራ ፡ ተጋብቷል ፡ ጠላት ፡ በደስታዬ (፫x)

አዝ፦ የደስታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ
ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከውስጤ ፡ ወስዶ
አመልከዋለሁ ፡ ከጠዋት ፡ ማታ
ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ (ጌታ) (፬x)

የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖ
ሃዘኔ ፡ ጠፋ ፡ እንደጉም ፡ በንኖ
አላማርርም ፡ አላንጐራጉር
ደስተኛ ፡ ነኝ ፡ ሁሌ ፡ በእግዚአብሔር (፫x)

አዝ፦ የደስታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ
ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከውስጤ ፡ ወስዶ
አመልከዋለሁ ፡ ከጠዋት ፡ ማታ
ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ (ጌታ) (፬x)

ማን ፡ ደስ ፡ ሊለው ፡ እኔ ፡ ልከፋ
በትንሽ ፡ ትልቁ ፡ ደስታዬ ፡ አይጠፋ
ለጠላት ፡ ወሬ ፡ ጆሮም ፡ አልሰጠው
ደስታዬ ፡ ፍጹም ፡ መቼም ፡ ማይወሰድ ፡ ነው (፫x)

አዝ፦ የደስታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ
ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከውስጤ ፡ ወስዶ
አመልከዋለሁ ፡ ከጠዋት ፡ ማታ
ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ (ጌታ) (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue