Dinq Neh (ድንቅ ፡ ነህ)

ያለፈውን ፡ ዘመን ፡ ታሪክ ፡ አገላብጠን
ሕይወትን ፡ ግራና ፡ ቀኙን ፡ ተመልክተን
አንድ ፡ እውነት ፡ ተረዳን ፡ ጠንቅቀን ፡ አውቀናል
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ብለናል

ለተቸገረው ፡ ሰው ፡ ፈጥነህ ፡ የምትደርስ
ሲጠሩህ ፡ የምትሰማ ፡ በእሳት ፡ የምትመልስ
የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ ዛሬስ ፡ መች ፡ ደክመሃል
በስምህ ፡ ተወራርደን ፡ ስንቱን ፡ ድል ፡ አድርገናል

አዝ:- ለአምላክነትህ ፡ በነፍስ ፡ ተወራርደን
ሁሉንም ፡ ጣልንና ፡ አንተን ፡ ተከተልን (፪x)
በዘመናት ፡ መሃል ፡ በድል ፡ ተሻግረናል
ልንክደው ፡ አንችልም ፡ ክንድህን ፡ አይተናል
ድንቅ ፡ ነህ ፡ ታደንቀናለህ (፬x)
ግሩም ፡ ነህ ፡ ታስገርመናለህ (፬x)

በችርነትህ ፡ አመታትን ፡ ለህዝብህ ፡ ታቀናጃለህ
ምድረ ፡ በዳው ፡ ስብ ፡ ይጠግባል ፡ ባሕሩን ፡ ታሻግራለህ
ከጠላት ፡ ዛቻ ፡ በሚገርም ፡ ታምራትህ ፡ ካመለጥን
በነፍሳችን ፡ ተወራርደን ፡ ይገባል ፡ አንተን ፡ ልናምን

አዝ:- ይውጣ ፡ እንጂ ፡ ያየታሪክ ፡ መዝገብ
ያደረከው ፡ በይፋ ፡ ይነበብ
እውነት ፡ ነው ፡ ዘመን ፡ ይናገራል
እግዚአብሔር ፡ ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ የታል (፪x)
ድንቅ ፡ ነህ ፡ ታደንቀናለህ (፬x)
ግሩም ፡ ነህ ፡ ታስገርመናለህ (፬x)

ሁሉን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥለን ፡ ተከተልንህ
እንደወደድክ ፡ አርገህ ፡ ይሄው ፡ ምራን ፡ አልንህ
ምች ፡ ከሰርን ፡ ታዲያ ፡ በብዙ ፡ አትርፈናል
በአንተ ፡ እንዳማረብን ፡ ጉዑዙ ፡ ይናገራል

በሚታየው ፡ ነገር ፡ ሕይወትን ፡ ሳንተምን
በእምነት ፡ ከቃልህ ፡ ጋር ፡ መራመድ ፡ መረጥን
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ክፋት ፡ ስምህ ፡ አድኖናል
ስትደግፈን ፡ ያዩ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ብለዋል

አዝ:- ለአምላክነትህ ፡ በነፍስ ፡ ተወራርደን
ሁሉንም ፡ ጣልንና ፡ አንተን ፡ ተከተልን (፪x)
በዘመናት ፡ መሃል ፡ በድል ፡ ተሻግረናል
ልንክደው ፡ አንችልም ፡ ክንድህን ፡ አይተናል
ድንቅ ፡ ነህ ፡ ታደንቀናለህ (፬x)
ግሩም ፡ ነህ ፡ ታስገርመናለህ (፬x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue