እንዲህ ፡ የምሆነው ፡ በዚህ ፡ ጉብዝናዬ
ያረፈበት ፡ ዓይኔ ፡ የወደደው ፡ ልቤ
በኢየሱስ ፡ ቁንጅና ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ያለው ፡ ሀሳቤ
ያረፈበት ፡ ዓይኔ ፡ የወደደው ፡ ቀልቤ
በኢየሱስ ፡ ቁንጅና ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ያለው ፡ ሃሳቤ
ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ይየው ፡ ይየው ፡ ጌታን ፡ ይየው
አንዴ ፡ ቀምሶ ፡ ካጣጣመው ፡ ሌላ ፡ አያሰኘው
ሌላውን ፡ ላልወድ ፡ ሌላዉን ፡ ላልሻ
በሌላ ፡ ላልታለል ፡ ሌላዉን ፡ ላልሻ
ተማርኬያለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x)
አመልከዋለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x)
ያገር ፡ ቆንጆ ፡ ነኝ ፡ ባዩ ፡ ከውዴ ፡ ሲተያዩ
ያመረ ፡ መሳይ ፡ ዉበቱ ፡ ዉዴ ፡ ይበልጠዋል ፡ በስንቱ
ያገር ፡ ቆንጆ ፡ ነኝ ፡ ባዩ ፡ ከየሱስ ፡ ሲተያዩ
ያመረ ፡ መሳይ ፡ ዉበት ፡ ዉዴ ፡ በዛበት ፡ በስንቱ
ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ይየዉ ፡ ይየው ፡ ጌታን ፡ ይየዉ
አንዴ ፡ ቀምሶ ፡ ካጣጣመዉ ፡ ሌላ ፡ አያሰኘዉ
እንዲህ ፡ የምሆነው (፪x)
የኢየሱስ ፡ ውበቱ ፡ ከሁሉ ፡ በልጦብኝ ፡ ነው
በዚህ ፡ ጉብዝናዬ ፡ ለዓለም ፡ ማልገዛው
ያዘጋጀው ፡ ክብር ፡ ከዓለም ፡ በልጦብኝ ፡ ነው (፪x)
አገር ፡ ሁሉ ፡ ያደነቀው ፡ ሰዓሊው ፡ የሳለው
አይ ፡ ሞኙ ፡ መች ፡ ገባው ፡ የኔን ፡ ቆንጆን ፡ አላየው
አገር ፡ ሁሉ ፡ ያደነቀው ፡ ሰዓሊው ፡ የሳለው
አይ ፡ ሞኙ ፡ መች ፡ ገባው ፡ ኢየሱሴን ፡ አላየው
ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ይየዉ ፡ ይየው ፡ ጌታን ፡ ይየዉ
አንዴ ፡ ቀምሶ ፡ ካጣጣመዉ ፡ ሌላ ፡ አያሰኘዉ
ውበትን ፡ ላላፈልግ ፡ ዓለምን ፡ ላልሻ
በዓለም ፡ ላላታለል ፡ ውበትን ፡ ላልሻ
አግኘቸዋለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x)
ወርሼዋለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x)
እንዲህ ፡ የምሆነው (፪x)
የኢየሱስ ፡ ውበቱ ፡ ከሁሉ ፡ በልጦብኝ ፡ ነው
በዚህ ፡ ጉብዝናዬ ፡ ለዓለም ፡ ማልገዛው
ያዘጋጀው ፡ ክብር ፡ ከዓለም ፡ በልጦብኝ ፡ ነው (፬x)