Yemetereda Yemetedegif (የምትረዳ ፡ የምታስደግፍ)

የምትረዳ ፡ የምትደግፍ ፡
የምታጽናና ፡ የምታሳርፍ
የማትለወጥ ፡ ሁሌ ፡ እውነተኛ
አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ ፡ ለኔ ፡ ጋደኛ
ወዳጅ ፡ እንዳንት ፡ የለም
ክብር ፡ ለዘለዓለም
ወዳጅ ፡ እንዳንት ፡ የለም
ክብር ፡ ለዘለዓለም

የልቤን ፡ ሃሳብ ፡ የማጫውትህ
የእኔ ፡ ማረፍያ ፡ ወዳጄ ፡ እንተ ፡ ነህ
ይኸው ፡ በዘመኔ ፡ ይህንን ፡ አየሁ
እንዳተ ፡ የሚሆን ፡ አንዳችም ፡ አጣሁ
ይኸው ፡ በዘመኔ ፡ ይህንን ፡ አየሁ
እንዳተ ፡ የሚሆን ፡ አንዳችም ፡ አጣሁ
፡ማን ፡ ይተካል ፡ ታዲያ ፡ በአንተ ፡ ቦታ
፡ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
፡ለማንም ፡ አልሰጥም ፡ የአንተን ፡ ቦታ
፡ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

አዳኝነትህ ፡ ተመችቶኛል
በቀን ፡ በሌሊት ፡ ልቤ ፡ ያስብሃል
አትሰለችም ፡ ሁሌ ፡ ባወራህ
ልቤም ፡ ስለዚህ ፡ አንተን ፡ ፈለገህ
አትሰለችም ፡ ሁሌ ፡ ባወራህ
ልቤም ፡ ስለዚህ ፡ አንተን ፡ ፈለገህ
፡ማን ፡ ይተካል ፡ ታዲያ ፡ በአንተ ፡ ቦታ
፡ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ ጌታ
፡ለማንም ፡ አልሰጥም ፡ የአንተን ፡ ቦታ
፡ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

ከሃዘኔ ፡ ስታጽናናኝ
መከራዬንም ፡ ስታስረሳኝ
የልቤ ፡ ደስታ ፡ አንተ ፡ ስትሆን
ይህን ፡ አይቼ ፡ ወደድኩህ ፡ አንተን
የልቤ ፡ ደስታ ፡ አንተ ፡ ስትሆን
ይህን ፡ አይቼ ፡ ወደድኩህ ፡ አንተን
፡ማን ፡ ይተካል ፡ ታዲያ ፡ በአንተ ፡ ቦታ
፡ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ ጌታ
፡ለማንም ፡ አልሰጥም ፡ የአንተን ፡ ቦታ
፡ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

ልቤ ፡ እንደ ፡ ድንግል ፡ ይወድሃል
አንተን ፡ ሲያስብህ ፡ ደስ ፡ ይለዋል
የእኔ ፡ ሙሽራ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
ፊትህን ፡ ሳይ ፡ ነው ፡ ፍጹ ፡ ደስታዬ
የእኔ ፡ ሙሽራ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
ፊትህን ፡ ሳይ ፡ ነው ፡ ፍፁም ፡ ደስታዬ
፡ማን ፡ ይተካል ፡ ታዲያ ፡ በአንተ ፡ ቦታ
፡ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ ጌታ
፡ለማንም ፡ አልሰጥም ፡ የአንተን ፡ ቦታ
፡ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue