Netsanet Assefa--Laiyeh Nafikalehu--Mesganaye Lante.mp3

በፊትህ ፡ መሆን ፡ ነው ፡ ደስታዬ
ድምጽህ ፡ ጣፋጭ ፡ ሆናል ፡ ለጆሮዬ
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ የለም ፡ የሚያረካኝ
እንተ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምተመችኝ
እንተ ፡ ነህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ምተመችኝ

ምሥጋናዬ ፡ ለአንተ ፡ ለጌታዬ
አምልኮዬ ፡ ለአንተ ፡ ለጌታዬ
ዝማሬዬ ፡ ለአንተ ፡ ለጌታዬ
አመልክሃለሁኝ ፡ በምሥጋና
አዜምልሃለሁ ፡ በምሥጋና
አቀኝልሃለሁ ፡ በምሥጋና

አንተን ፡ እንጂ ፡ ምንም ፡ አልፈልግም
እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ ማንም ፡ የለም
ለኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ ወዳጄ ፡ ነህ
በዚህ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ ላመስግንህ
በዚህ ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ ላመስግንህ

የሚጠቅመኝ ፡ የለም ፡ በዚህች ፡ ምድር ፡
ከአንተ ፡ በስተቅር ፡ ከእግዚአብሔር
አስፍቼ ፡ እሄዳለሁ ፡ በመንገድህ
ተድላ ፡ ሆኖልኛል ፡ ትህዛዝህ
ሰላም ፡ ሆኖልኛል ፡ ትህዛዝህ

ነፍሴ ፡ ዝም ፡ ብለሽ ፡ አመስግኚው
እግዚአብሔር ፡ አምላክሽን ፡ እርሱን ፡ ወደጂው
ልጅን ፡ በመሰዋት ፡ አቅርቦሻል ፡
በፍቅሩ ፡ ሁልግዜ ፡ ያረካሻል
በፍቅሩ ፡ ሁልግዜ ፡ ያረካሻል

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue