Netsanet Assefa--Laiyeh Nafikalehu--Hallelujah.mp3

አምላኬ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርግሃለሁ
ስምህን ፡ ለዘላላም ፡ እባርካለሁ
እጅግ ፡ የተመሰግንህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነህ
ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የሌለው

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡

እግዚአብሔር ፡ ርህሩህና ፡ መሐሪ ፡ ነው
ከቁጣ ፡ የራቀ ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው
ለሚታገሱት ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቸር ፡ ነው
ምህረቱ ፡ ያምላካችን ፡ በስራው ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ነው

በቃሎችህ ፡ አቤቱ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ
በስራህም ፡ በመንግድህ ፡ ሁሉ ፡ ጽድቅ ፡ ነህ
ተስፋ ፡ ለሚያደርጉህ ፡ ሁሉ ፡ አንተ ፡ እጅህን ፡ ትከፍታለህ
ሕይወት ፡ ላለውም ፡ ሁሉ ፡ መልካምን ፡ ታጠግባለህ

መንግሥትህ ፡ የዘለዓለም ፡ መንግሥት ፡ ናት
እግዚአብሔር ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ግዛት
አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ ያመስግኑሃል
ቅዱሳንህም ፡ ሁሉ ፡ አንተኑ ፡ ይባርኩሃል

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue