Gena (ገና)

ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ (ገና ፡ ገና)
ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ አዎ ፡ ገና ፡ ገና
የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ መች ፡ አለቀና ፡ (በእኔ ፡ በእኔ ፡ በእኔ)
የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ መች ፡ አለቀና (፪x)

እንዲሁ ፡ በዋዛ ፡ መሞት ፡ አለ ፡ ወይ ፡ (መሞት ፡ አለ ፡ ወይ)
ሰውስ ፡ ስላወራ ፡ መሞት ፡ አለ ፡ ወይ ፡ (የለም ፡ የለም ፡ የለም)
ስለ ፡ እኔ ፡ የሚሟገት ፡ አለ ፡ በሠማይ
አለ ፡ በሠማይ (፪x)

ክብሩን ፡ ሲጨምርብኝ
ሞገሱን ፡ ሲደርብብኝ
ፀጋውን ፡ ሲያበዛልኝ
ኢህንን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ቀና
ሞቷል ፡ እያለ ፡ በከተማው ፡ ሲያወራ

እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋራ
እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ ከጌታ ፡ ጋራ
በክብሩ ፡ ወጣሁ ፡ ከአባቴ ፡ ጋራ
በሞገስ ፡ ገባሁ ፡ ከአባቴ ፡ ጋራ

ኑሮዬም ፡ ሕይወቴም ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ናት ፡ (በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ናት)
እስትንፋሴም ፡ ሁሉ ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ናት ፡ (ናት)
ታሪኬ ፡ አላበቃም ፡ ዞር ፡ በል ፡ አንተ ፡ ጠላት
ዞር ፡ በል ፡ አንተ ፡ ጠላት (፪x)

ክብሩን ፡ ሲጨምርብኝ
ሞገሱን ፡ ሲደርብብኝ
ፀጋውን ፡ ሲያበዛልኝ
ኢህንን ፡ ያየ ፡ ጠላቴ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ቀና
ሞቷል ፡ እያለ ፡ በከተማው ፡ ሲያወራ

እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋራ
እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ ከጌታ ፡ ጋራ
በክብሩ ፡ ወጣሁ ፡ ከአባቴ ፡ ጋራ
በሞገስ ፡ ገባሁ ፡ ከአባቴ ፡ ጋራ

ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ (ገና ፡ ገና)
ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ አዎ ፡ ገና ፡ ገና
የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ መች ፡ አለቀና ፡ (በእኔ ፡ በእኔ ፡ በእኔ)
የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ መች ፡ አለቀና (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue