Kiburena Qidus New (ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ነው )

ፅድቅና ፡ መንግሥትህ ፡ እንደምን ፡ ያምራሉ
ከአንተ ፡ ወድያ ፡ ሕይወት ፡ ለምን ፡ ያሰኛሉ
የአባትነትህ ፡ ፍቅርህ ፡ በኢየሱስ ፡ ያየነው
ማርኮ ፡ አስቀርቶናል ፡ ኑሮዋችን ፡ የአንተ ፡ ነው (፪x)

አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል
ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም
አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x)

ሥራህን ፡ እያየን ፡ እናደንቅሀለን
ሁልጊዜ ፡ ፍቅርህን ፡ ጌታ ፡ እናስባለን
መንፈስና ፡ ሥጋ ፡ ነፍሳችን ፡ ተስማምተው
ያመሰግኑሃል ፡ ክበር ፡ ጌታ ፡ ብለው (፪x)

አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል
ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም
አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x)

ውለታህ ፡ አለብን ፡ ከልብ ፡ የማይጠፋ
እኛን ፡ የረዳኸን ፡ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ
ከቶ ፡ ምን ፡ አለና ፡ ለእኛ ፡ ያላደረከው
መድኃኒታችን ፡ ሆይ ፡ ክብራችን ፡ ከአንተ ፡ ነው (፪x)

አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል
ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም
አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x)

ከፀሐይ ፡ ሰባት ፡ እጅ ፡ ድምቀህ ፡ ትታያለህ
ሁለንተናህ ፡ ውብ ፡ ነው ፡ ምንም ፡ አልጐደለህ
ለግርማዊነትህ ፡ ክብር ፡ እንሰግዳለን
ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ እንዘምራለን (፪x)

አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል
ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም
አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፬x)

ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም
አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x)

አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል
ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም
አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue