(ብቻውን ፡ ተዓምር ፡ የሚያደርግ ፡ ችግረኛን ፡ የሚታደግ
እንቆቅልሽ ፡ የሚፈታ ፡ ኢየሱስ ፡ የኛ ፡ ጌታ) (፪x)
ጠላት ፡ ሲሽቀዳደም ፡ ሊመታን ፡ በጡጫ
ቅጥሩን ፡ ሰበረልን ፡ ሆነልን ፡ ማምለጫ
እንናገር ፡ ብንል ፡ ብዙ ፡ እናወራለን
በዝች ፡ አጭር ፡ እድሜ ፡ ምረቱን ፡ ስላየን
በዝች ፡ አጭር ፡ ዘመን ፡ ማዳኑን ፡ ስላየን
አዝ
ብቻውን ፡ ተዓምር
ኃጢአታችን ፡ በዝቶ ፡ ስንባዝን ፡ በዓለም
ሕይወት ፡ ሆነን ፡ የሱስ ፡ ሊያኖረን ፡ ዘለዓለም
ምን ፡ እንመልሳለን ፡ ከምሥጋና ፡ ሌላ
(በጭንቃችን ፡ ስዓት ፡ ለሆነን ፡ ከለላ
በጭንቃችን ፡ ስዓት ፡ ለሆነን ፡ ከለላ)
አዝ
ብቻውን ፡ ተዓምር
የአናብስትን ፡ አፍ ፡ ጥርስ ፡ እየሰበረ
ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እያሸጋገረ
በደመናው ፡ አምድ ፡ ዘወትር ፡ ይመራናል
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሆነን ፡ አረ ፡ ምን ፡ ጐሎናል
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሆነን ፡ አረ ፡ ምን ፡ ጐሎናል
አዝ
ብቻውን ፡ ተዓምር
ጠላት ፡ ሲሽቀዳደም ፡ ሊመታን ፡ በጡጫ
ቅጥሩን ፡ ሰበረልን ፡ ሆነልን ፡ ማምለጫ
እንናገር ፡ ብንል ፡ ብዙ ፡ እናወራለን
በዝች ፡ አጭር ፡ እድሜ ፡ ምረቱን ፡ ስላየን
በዝች ፡ አጭር ፡ ዘመን ፡ ማዳኑን ፡ ስላየን
አዝ
ብቻውን ፡ ተዓምር