Ethiopia (ኢትዮጵያ)

አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ ሀገሬ ፡ እጆችሽን ፡ የምትዘረጊበት
ሰዓቱ ፡ ደርሷል ፡ እንባ ፡ ሚደርቅበት ፡ ካፈርሽ
ሰላም ፡ ይታጨዳል ፡ ከወንዝሽ
ዓለም ፡ ይባረካል ፡ ዓለም ፡ ይባረካል (፪x)

አያለሁ ፡ አዲስ ፡ ቀን ፡ ከደመናው ፡ ማዶ
ብርሃን ፡ ሲወጣልሽ ፡ ጨለማውን ፡ ቀዶ
የራቁት ፡ ልጆችሽ ፡ ይሰበሰባሉ
እውነትም ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃያል ፡ ነው ፡ እያሉ
ባማሩት ፡ መቅደሶች ፡ ወንጌል ፡ ይሰበካል
ህጻን ፡ ሽማግሌው ፡ ለአምላክ ፡ ክብር ፡ ያመጣል
እግዚአብሔርም ፡ ቃሉን ፡ በታምር ፡ ያጸናል
ሊሰራ ፡ ሲወጣ ፡ ማን ፡ ይቃወመዋል ፡ ማን ፡ የከለክላል

አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ ሀገሬ ፡ እጆችሽን ፡ የምትዘረጊበት
ሰዓቱ ፡ ደርሷል ፡ እንባ ፡ ሚደርቅበት ፡ ካፈርሽ
ሰላም ፡ ይታጨዳል ፡ ከወንዝሽ
ዓለም ፡ ይባረካል ፡ ዓለም ፡ ይባረካል

እውቀትና ፡ ጥበብ ፡ ከአምላክ ፡ የተዋሉ
ኃጢያትን ፡ ጠልተው ፡ ለጽድቅ ፡ የሚኖሩ
ልዋይና ፡ ዝና ፡ ከቶ ፡ ማይገዛቸው
ለፍርድና ፡ ለእውነት ፡ ቅናት ፡ የበላቸው
ልጆች ፡ አሉሽ ፡ ገና ፡ ተግተው ፡ የሚነሱ
ለምስኪኑ ፡ መውደቅ ፡ ከልብ ፡ የሚሳሱ
የተገባልሽ ፡ ቃል ፡ በእርግጥ ፡ ይፈጸማል
አምላክሽ ፡ ሊያድንሽ ፡ ሊታደግሽ ፡ ወጥቷል ፡ ሊታደግሽ ፡ ወጥቷል

አዝ:- ኢትዮጵያ ፡ ሀገሬ ፡ እጆችሽን ፡ የምትዘረጊበት
ሰዓቱ ፡ ደርሷል ፡ እንባ ፡ ሚደርቅበት ፡ ካፈርሽ
ሰላም ፡ ይታጨዳል ፡ ከወንዝሽ
ዓለም ፡ ይባረካል ፡ ዓለም ፡ ይባረካል (፫x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue