መድኃኒቴ

እጅግ ፡ ከሚያስፈራው ፡ ከገሃነም ፡ እሳት
መድሃኒት ፡ የሆንከኝ ፡ ነፍሴን ፡ የታደካት
ወደ ፡ ውስጤ ፡ ገብተህ ፡ ፈውስን ፡ አግኝቻለሁ
ለዘለዓለሙ ፡ ሳልሰጋ ፡እኖራለሁ (፪x)

አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኦሆሆ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም ፡ አሃሃ
እውነተኛ ፡ አዳኝ ፡ ኦሆሆ ፡ ፈዋሽ ፡ የሆንከኝ ፡ አሃሃ
ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም (፪x)
ሃሌሉያ

መከራ ፡ ዙሪያዬን ፡ ሲያስፈራ ፡ ሲከበኝ
ቀር ቦ ፡ የነበረ ፡ ወዳጅም ፡ ሲሸሸኝ
ያለኝ ፡ የመሰለኝ ፡ ከጄ ፡ ሲጠፋብኝ
አልጥልሽም ፡ እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አልከኝ (፪x)

አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኦሆሆ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም ፡ አሃሃ
እውነተኛ ፡ አዳኝ ፡ ኦሆሆ ፡ ረዳት ፡ የሆንከኝ ፡ አሃሃ
ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም (፪x)
ሃሌሉያ

ዛሬም ፡ ወደፊት ፡ ለሚያስፈልገኝ
ማንስ ፡ ሊያበረታ ፡ ማንስ ፡ ሊያግዘኝ
ሰላምም ፡ መፍትሔም ፡ መሆን ፡ የሚቻለው
እውነተኛ ፡ ተስፋ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ መድሃኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኦሆሆ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም ፡ አሃሃ
እውነተኛ ፡ አዳኝ ፡ ኦሆሆ ፡ ፈዋሽ ፡ የሆንከኝ ፡ አሃሃ
ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ ሌላማ ፡ የለኝም (፪x)
ሃሌሉያ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue