አዝ፦ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ሆነልኝ (፪x)
እንደ ፡ ጠላቴ/ከሳሼ ፡ አልሆነብኝም
ጌታ ፡ አሸነፈልኝ ፡ ሃሌሉያ (፪x)
ተሻገርኩኝ (፪x) ፡ አቅፎ ፡ ደግፎ ፡ አሻገረኝ
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አዎ
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አዎ
የማደርገው ፡ መላ ፡ ቢጠፋብኝ
በሬን ፡ ዘጋሁ ፡ ጊታ ፡ ብዬ ፡ ጮህኩኝ
ድንገት ፡ መጥቶ ፡ ሰላም ፡ ይሁን ፡ ብሎ
አበሳዬን ፡ ከላይ ፡ አንከባሎ ፤ አሳረፈኝ (፫x)
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እስራቴን ፡ የፈታ
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሰንሰለቴን ፡ የፈታ
አዝ፦ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ሆነልኝ (፪x)
እንደ ፡ከሳሼ ፡ አልሆነብኝም
ጌታ ፡ አሸነፈልኝ ፡ ሃሌሉያ
ተሻገርኩኝ (፪x) ፡ አቅፎ ፡ ደግፎ ፡ አሻገረኝ
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አዎ
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አዎ
ጽኑ ፡ ቅጥር ፡ ዙሪያቸውን ፡ ቀጥረው
እንዳላልፍ ፡ በመንገዴ ፡ ቆመው
አላስገባም ፡ ያሉኝ ፡ ጠላቶቼ
በአንዴ ፡ ጩኸት ፡ ወደቁ ፡ ከእግሮቼ
አዩ ፡ ዐይኖቼ (፫x)
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ጠላቶቼን ፡ የመታ
ይሄ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ከሳሾቼን ፡ የመታ
አዝ፦ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ሆነልኝ (፪x)
እንደ ፡ከሳሼ ፡ አልሆነብኝም
ጌታ ፡ አሸነፈልኝ ፡ ሃሌሉያ
ተሻገርኩኝ (፪x) ፡ አቅፎ ፡ ደግፎ ፡ አሻገረኝ
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አዎ
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አዎ
ያጠላቴ ፡ ጦሩን ፡ ሰበቀብኝ
ከግድግዳ ፡ ጋራ ፡ ሊያጣብቀኝ
ቀስቱን ፡ ሁሉ ፡ ሰባበረውና
አስመለጠኝ ፡ ጋሻ ፡ ሆነኝና
ኢየሱስ ፡ ገናና (፫x)
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ጠላቶቼን ፡ የመታ
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ከሳሾቼን ፡ የመታ
አዝ፦ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ሆነልኝ (፪x)
እንደ ፡ከሳሼ ፡ አልሆነብኝም
ጌታ ፡ አሸነፈልኝ ፡ ሃሌሉያ
ተሻገርኩኝ (፪x) ፡ አቅፎ ፡ ደግፎ ፡ አሻገረኝ
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አዎ
እጄን ፡ ይዞኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እጄን ፡ ይዞኝ ፡ አዎ (፪x)