አልጥልህም ፡ አልተውህም (Altelehem Altewehem)

"በሕይወትህ ፡ ዕድሜ ፡ ሁሉ ፡ ማንም ፡ አይቋቋምህም
ከሙሴ ፡ ጋር ፡ እንደሆንኩ ፡ እንዲሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እሆናለሁ
አልጥልህም ፡ አልተውህም ፣ አልጥልህም ፡ አልተውህም"

ከሙሴ ፡ ጋር ፡ እንደነበርኩ ፡ ከአንተ ፡ ጋርም ፡ እሆናለሁ
ብቻ ፡ በርታ ፡ ጽና ፡ ልጄ ፡ ሁሉን ፡ መልካም ፡ አደርጋለሁ
ምንም ፡ ነገር ፡ ዓይነካህም ፡ እርግማን ፡ አይደርስብህም
በጠላት ፡ ላይ ፡ ትጫማለህ ፡ ዘንዶ ፡ እባቡን ፡ ትረግጣለህ

አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ
እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x)
አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ
ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ
እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ
አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ

ለዘላለም ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ና ፡ በፊቴ ፡ ተመላለስ
የገባሁልህን ፡ ተስፋ ፡ አምጥቻለሁና ፡ ለአንተ ፡ በዚህ
ስለዚህ ፡ አትጠራጠር ፡ ጸንተህ ፡ ቁም ፡ በእኔ ፡ ተማምነህ
የማልጥል ፡ የማልተው ፡ አምላክ ፡ አለሁ ፡ እኔ ፡ በአጠገብህ

አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ
እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x)
አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ
ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ
እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ
አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ

በሕይወትህ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ሊቋቋሙህ ፡ እንዳይችሉ
ጠላቶችህን ፡ መታለሁ ፡ በፊት ፡ ለፊትህ ፡ ጥላለሁ
በክንዶቼ ፡ ትያዛለህ ፡ ብቻ ፡ ታመን ፡ ትድናለህ
ለዘላለም ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ ከእቅፌ ፡ ማን ፡ ሊያወጣህ

አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ
እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x)
አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ
ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ
እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ
አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ

እንደቃሌ ፡ እንዲሁ ፡ ነኝ ፡ አደርጋለሁ ፡ ከቶ ፡ አልዋሽም
የተናገርኩትን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽማለሁ ፡ እንድ ፡ አይቀርም
ከእኔ ፡ በቀር ፡ አምላክ ፡ የለም ፡ ማንም ፡ በምድር ፡ በሰማይ
ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ አልለወጥ ፡ ለዘላለም ፡ ኤልሻዳይ

አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ
እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x)
አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ
ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ
እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ
አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ

እስራኤልን ፡ ትመራለህ ፡ ዮርዳኖስን ፡ ትከፍላለህ
ከግራ ፡ ቀኝ ፡ አለሁ ፡ እኔ ፡ ታወጣለህ ፡ ታገባለህ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ እንዳለሁኝ ፡ በህዝቡ ፡ ዘንድ ፡ ይታወቃል
ዘመንህን ፡ ባርኬያለሁ ፡ ገለአድን ፡ ትወርሳለህ
ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንዳለሁኝ ፡ በህዝቡ ፡ ዘንድ ፡ ይታወቃል
ዘመንህን ፡ ባርኬያለሁ ፡ ክብሬ ፡ በላይህ ፡ ይታያል

አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ
እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x)
አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ
ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ
እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ
አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ

አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ
ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ
እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የቅዱሳን ፡ ተስፋ
እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የኢትዮጵያ ፡ ተስፋ
እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue