Bedelin Yikir Yemil (በደልን ፡ ይቅር ፡ የሚል)

በደልን ፡ ይቅር ፡ የሚል ፡ አመጻን ፡ የሚያሳልፍ
ከጥፋት ፡ ሊያድናቸው ፡ በሕዝቡ ፡ ላይ ፡የሚሰፍፍ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ ማነው ፡ ምህረቱ ፡ የበዛ?
ቅዱሳንህ ፡ ሲሰደዱ ፡ መከራውም ፡ ሲበዛ

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ

የእግዚአብሔር ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፡ተፅፏል ፡ ህዝቡ ፡ ነው !
ሊያመልከው ፡ ሊያገለግለው ፡ ከግብጽ ፡ አገር ፡ ያፈለሰው
አርነቱን ፡ በባርነት ፡ ሊተካ ፡ የሚከጅለው
"ይገባኛል " ፡ የሚል ፡ ማነው ? ሕዝቡ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው!

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ

እስከዛሬ ፡ከብረሃል ፡ በአህዛብ ፡ ተፈርተሃል
የጠላትን ፡ እርግማን ፡ በረከት ፡ አድርገሃል
የአሳዳጁን ፡ ፈረሶች ፡ በባሕር ፡ አስጥመሃል
በክንድህ ፡ ተከላክለህ ፡ ርስትህን ፡ ጠብቀሃል

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue