• 7
  • 0
  • 0
  • 0
  • 0

Yehew (ይኸው )

ከስምህ ፡ ሌላ ፡ ቀንበር ፡ አይጫነኝ
ከፍቅርህ ፡ ሌላ ፡ ዕዳ ፡ አይኑርብኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ አግዘኝ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ በፍቅርህ ፡ አኑረኝ (፪x)

አዝ፦ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ወደጄ ፡ ለአንተ ፡ አስገዛለሁ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ፈቅጄ ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ

የልቤን ፡ ሃሳብ ፡ መርምረህ ፡ ታውቃለህ
አረማመዴን ፡ ትመለከታለህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ፍፁም ፡ ህግህ ፡ ይግዛኝ
የተሰወረ ፡ ኀጢአት ፡ እንዳይገዛኝ (፪x)

አዝ፦ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ፈቅጄ ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ
ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ወድጄ ፡ ልቤን ፡ አስገዛለሁ

ፍቅርህ ፡ ፍፁም ፡ ነው ፡ ነፍስን ፡ ይመልሳል
ስራትህ ፡ ልብን ፡ ደስ ፡ ያሰኛል
ልጠብቀው ፡ ለቃልህ ፡ እተጋለሁ
የዚያን ፡ ጊዜ ፡ ፍፁም ፡ እሆናለሁ (፪x)

አዝ፦ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ፈቅጄ ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ፈቅጄ ፡ ወድጄ ፡ ልቤን ፡ አስገዛለሁ

ትእዛዝህ ፡ ብሩህ ፡ ዐይንንም ፡ ያበራል
ፍራትህ ፡ ንጹህ ፡ ዘላለም ፡ ይኖራል
ከከበረ ፡ እንቁ ፡ ይመረጣል
ከማር ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ ይወደዳል (፪x)

አዝ፦ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ወድጄ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ፈቅጄ ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ወድጄ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ
ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ፈቅጂ ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ፈቅጄ ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ወድጄ ፡ ልቤን ፡ አስገዛለሁ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ፈቅጄ ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ
ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ
ወድጄ ፡ ልቤን ፡ አስገዛለሁ
ይኸው

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue