Geta Hoy (ጌታ ፡ ሆይ ).mp3

አዝ፦ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ መንገዴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ ሃገር ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ መንገዱ ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ

ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ጐስቋላነቴን
የማልረባ ፡ ልጅ ፡ መሆኔን
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆነህ ፡ ካልረዳኽኝ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ መንገዴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ ሃገር ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ መንገዱ ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ

የእምነቴ ፡ ድጋፍ ፡ ነህና
ልመርኮዝህ ፡ ጌታዬ ፡ ና
አልመካም ፡ በመቆሜ
ካልሆንክ ፡ አንተ ፡ አጠገቤ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ መንገዴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ ሃገር ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ መንገዱ ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ

ዓለማመኔን ፡ እርዳው ፡ ባክህ
በኑሮዬ ፡ እንዳስከብርህ
እምነቴ ፡ ከስራ ፡ ተለይቶ
አንዳልጠፋ ፡ መንገዴ ፡ አንተን ፡ ስቶ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ መንገዴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ ሃገር ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ መንገዱ ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ

ሲከፋኝ ፡ አጽናናኝ ፡ መድሃኒቴ
ስደክም ፡ ደግፈኝ ፡ በሕይወቴ
ማን ፡ አለኝ ፡ አለ ፡ አንተ ፡ አለኝታዬ
እስከጽዮን ፡ ድረስ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ መንገዴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ ሃገር ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን ፡ አደራ
የምሄድበት ፡ መንገዱ ፡ ሩቅ ፡ ነው ፡ አደራ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue