አሳረፈኝ (Asarefegn) - ነጻነት ፡ አሰፋ

የእኔ ፡ ነሽ ፡ ብሎ ፡ አሳረፈኝ
የእኔ ፡ ነሽ ፡ ብሎ ፡ አሳረፈኝ
የእርሱ ፡ አድሮጐኛል ፡
ጌታዬ ፡ አሳርፎኛል ፡
የእርሱ ፡ አድሮጐኛል ፡
አሳርፎኛል

ሃሳቤን ፡ ሁሉ ፡ ወዲያ ፡ ትቼ
ለአላማህ ፡ ተነስቼ ፡
በጐነትክን ፡ ጽድቅህን ፡ ላውራ
አንተ ፡ አለህ ፡ ከኔ ፡ ጋራ
እንደኔማ ፡ እንደ ፡ ሃሳቤ ፡
አመስገኜ ፡ መች ፡ ጠገቤ
ከእንግዲህ ፡ የምኖረው
ለሞተልኝ ፡ ለእርሱ ፡ ነው

፡ ማን ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ነገን ፡ የሚያውቀው
፡ ትንፋሼን ፡ መንዴን ፡ እርሱ ፡ የያዘው
፡ እግዚአብሔር ፡ የሰራት ፡ ይህቺ ፡ ቀን ፡ ዛሬ ፡ ናት
፡ በእርሱ ፡ ደስ ፡ እያለኝ ፡ ሃሴት ፡ ላድርግባት ፡
፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ አድርጐ ፡ ፈጥሮኛል ፡
፡ በፈጥረኝ ፡ አምላክ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ አድርጐ ፡ ፈጥሮኛል ፡
፡ በፈጠረኝ ፡ ጌታ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
፡ እኔ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኔ ፡ በፈጣሪዬ ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኔ ፡ በመድሃኒቴ ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኒ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ

የእኔ ፡ ነሽ ፡ ብሎ ፡ አሳረፈኝ
የእኔ ፡ ነሽ ፡ ብሎ ፡ አሳረፈኝ
የእርሱ ፡ አድሮጐኛል ፡
ጌታዬ ፡ አሳርፎኛል
የእርሱ ፡ አድሮጐኛል ፡
አሳርፎኛል ፡


እርሱ ፡ ይሁን ፡ ብሎ ፡ በፈጠራቸው
እራሱ ፡ እይቶ ፡ መልካም ፡ ባላቸው
አምላኬ ፡ ፍቅሩ ፡ በዚህ ፡ አለበቃውም
የልቡን ፡ ሃሳብ ፡ አልገለጡትም
ፍቅሩን ፡ ለኔ ፡ እንዲህ ፡ ገለጠ ፡ ሃሃ
ራሱን ፡ መባ ፡ አድርጐ ፡ ስለኔ ፡ ሰጠ
አምላክ ፡ ሰው ፡ ሆኖ ፡ ምድር ፡ መጣና ፡ ሃሃ
የእርሱ ፡ አደርገኝ ፡ ሞተልኝና ፡

፡ እኔ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኔ ፡ በፈጣሪዬ ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኔ ፡ በመድሃኒቴ ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኒ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ

በፈቴ ፡ ያለውን ፡ ተራራ ፡ እያየሁኝ ፡
ረዳት ፡ እንደሌለው ፡ ምን ፡ ተስፋ ፡ አስቆረጠኝ
ተራራን ፡ የሰራ ፡ ረዳቴ ፡ ይመጣና
መንገድ ፡ ያደርግልኛል ፡ ሜዳ ፡ ሁን ፡ ይልና
እርሱ ፡ አማኑኤል ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ መተከዝ ፡ ምንድ ፡ ነው
እርሱ ፡ አማኑኤል ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ መተከዝ ፡ ምንድ ፡ ነው

የእኔ ፡ ነሽ ፡ ብሎ ፡ አሳረፈኝ
የእኔ ፡ ነሽ ፡ ብሎ ፡ አሳረፈኝ
የእርሱ ፡ አድሮጐኛል ፡
ጌታዬ ፡ አሳርፎኛል
የእርሱ ፡ አድሮጐኛል ፡
አሳርፎኛል ፡

ምህረት ፡ ቸርነቱን ፡ ፍቅሩን ፡ አይቻለሁ
ለሚታመኑበት ፡ መከታ ፡ ጋሻ ፡ ነው
አስተማማኝ ፡ አምባ ፡ እረኛ ፡ እርሱ ፡ ነው
መንጋዎቹን ፡ ከእጁ ፡ የማይነጠቀው
ደስ ፡ ይበለኝ ፡ እንዲ ፡ በዚህ ፡ ታላቅ ፡ ጌታ
ደስታን ፡ ባስታጠቀኝ ፡ በሰቆቃ ፡ ፈንታ
ሕይወትን ፡ በሰጠኝ ፡ ሞቶ ፡ በኔ ፡ ፈንታ ፡

፡ እኔ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኔ ፡ በፈጣሪዬ ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኔ ፡ በመድሃኒቴ ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ
፡ እኒ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ደስ ፡ እሰኛለሁ

সম্প্রতি দ্বারা শোনা

0 মন্তব্য
    কোন মন্তব্য পাওয়া যায়নি

:: / ::
::
/ ::

কিউ