Bealem Kemigegn (በዓለም ፡ ከሚገኝ).mp3

አዝ፦ በዓለም ፡ ከሚገኝ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ይልቅ
ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መነቀፍን ፡ የሚበልጥ
ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቷልና
ሙሴ ፡ ጌታን ፡ አከበረው ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና

ለጊዜው ፡ በኀጢአት ፡ ከሚገኝ ፡ ደስታ ፡ ይልቅ
ለጌታ ፡ መነቀፍ ፡ እጅግ ፡ እንደሚበልጥ
ታውቆት ፡ ክብሩን ፡ ተወ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተማምኖ
ጌታም ፡ አልተወውም ፡ አየሁ ፡ ልጄ ፡ ብሎ

አዝ፦ በዓለም ፡ ከሚገኝ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ይልቅ
ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መነቀፍን ፡ የሚበልጥ
ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቷልና
ሙሴ ፡ ጌታን ፡ አከበረው ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና

የማይታየውን ፡ በእምነት ፡ እያየ
የዓለምን ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ ጌታ ፡ ጣለ
ጌታም ፡ አከበረው ፡ ልጁን ፡ አልተወውም
ፀጋን ፡ አለበሰው ፡ ዓለም ፡ የማያየውን

አዝ፦ በዓለም ፡ ከሚገኝ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ይልቅ
ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መነቀፍን ፡ የሚበልጥ
ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቷልና
ሙሴ ፡ ጌታን ፡ አከበረው ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና

እምነቴን ፡ በስራ ፡ እንድገልጠው
የግለት ፡ መንፈስህን ፡ በሕይወቴ ፡ አብዛው
እስከሞትም ፡ እንኳ ፡ ለስምህ
ለመጋደል ፡ አብቃኝ ፡ እባክህ

አዝ፦ በዓለም ፡ ከሚገኝ ፡ ብዙ ፡ ክብር ፡ ይልቅ
ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መነቀፍን ፡ የሚበልጥ
ብድራቱን ፡ ትኩር ፡ ብሎ ፡ አይቷልና
ሙሴ ፡ ጌታን ፡ አከበረው ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

በተመጣጣኝ በጀት እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads:: / ::
::
/ ::

Queue