Libih Tsinu Yihun (ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን)

አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር
በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x)

ተድላና ፡ ደስታ ፡ መጽናናት ፡ በረከት
ሁሌ ፡ መንደላቀቅ ፡ በተሟላ ፡ ሕይወት
እንደዚህ ፡ አይደለም ፡ እንዲህ ፡ አትመልከት
ክርስትና ፡ አንዳንዴ ፡ መከራም ፡ አለበት

አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር
በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x)

የጨለማው ፡ ስልጣን ፡ ጥላውን ፡ ዘርግቶ
ጠላት ፡ ኃይሉን ፡ ሲያሳይ ፡ እጅግ ፡ ተቆጥቶ
በበትር ፡ ሲመታህ ፡ ሆምጣጤ ፡ ሲያጠጣህ
በመስቀሉ መንገድ ፡ ወንድሜ ፡ አይክፋህ

አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር
በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x)

ማምለጫ ፡ ስታሻ ፡ ቀዳዳ ፡ ስትፈልግ
ጭላንጭሉስ ፡ እንኳን ፡ ሲደፈን ፡ ሲመረግ
በወህኒ ፡ ተጥለህ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲረሳህ
የሕይወትህ ፡ ጌታ ፡ የሚረሳህ ፡ አይምሰልህ

አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር
በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x)

በምስራቹ ፡ ቃል ፡ በወንጌል ፡ ተሟገት
ልብህ ፡ ሰፊ ፡ ይሁን ፡ አርቀህ ፡ ተመልከት
ለማያልፈው ፡ እርስት ፡ ለአገርህ ፡ ተዋግተህ
በላይ ፡ እንገናኝ ፡ ደምህን ፡ አጥለቅልቀህ

አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር
በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x)

最近聴いた人

0 コメント
    コメントがありません

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::