Abertetognal (አበርትቶኛል)

አበርትቶኛል ፡ ጉልበቴ ፡ እጅግ ፡ ዝሎ
አሻግሮኛል ፡ ዮርዳኖስን ፡ ከፍሎ
እንዴት ፡ እረሳዋለሁ ፡ እግዚአብሔርን
ከበረት ፡ አውጥቶ ፡ ከግብጽ ፡ ያወጣኝን

አዝ፦ ላመስግነው (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)
ልቀኝለት ፡ ልቀኝለት ፡ ልስገድለት
በሕይወት ፡ ላቆመኝ ፡ ላዳነኝም ፡ ከሞት (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)

አስቀድሞ ፡ አውቆኛል ፡ በሆድ ፡ ሳልሰራ
መርጦኛል ፡ እራሱ ፡ ጨለማዬም ፡ በራ
ዓይኖቼም ፡ ማዳኑን ፡ እዩ ፡ ተዓምራቱን
ስለ ፡ ፍቅርም ፡ ብሎ ፡ የሰዋውን ፡ ልጁን

አዝ፦ ላመስግነው (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)
ልቀኝለት ፡ ልቀኝለት ፡ ልስገድለት
በሕይወት ፡ ላቆመኝ ፡ ላዳነኝም ፡ ከሞት (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)

አስጨናቂዎቼ ፡ ሰልፍ ፡ አብዝተውብኝ
ከአምላኬ ፡ ጉያ ፡ መስሏቸው ፡ የሚነጥቁኝ
ግን ፡ የማያንቀላፋው ፡ ተግቶ ፡ የሚጠብቀኝ
በዙሪያዬ ፡ ካሉት ፡ በእውነት ፡ አሳረፈኝ

አዝ፦ ላመስግነው (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)
ልቀኝለት ፡ ልቀኝለት ፡ ልስገድለት
በሕይወት ፡ ላቆመኝ ፡ ላዳነኝም ፡ ከሞት (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ በፍቅሩ ፡ ይዞኛል
እንዳልወድቅም ፡ ምርኩዝ ፡ ድጋፍ ፡ ሆኖልኛል
ምን ፡ ልበለው ፡ እኔስ ፡ ውለታው ፡ በዛብኝ
ሕያዋን ፡ ሁላችሁ ፡ እስኪ ፡ አመስግኑልኝ

አዝ፦ ላመስግነው (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)
ልቀኝለት ፡ ልቀኝለት ፡ ልስገድለት
በሕይወት ፡ ላቆመኝ ፡ ላዳነኝም ፡ ከሞት (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ባለውለታዬ ፡ ነው (፪x)

সম্প্রতি দ্বারা শোনা

0 মন্তব্য
    কোন মন্তব্য পাওয়া যায়নি

:: / ::
::
/ ::

কিউ