Mesgna Melkam (ምሥጋና ፡ መልካም ፡ ነው)

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ
ለጌታ ፡ ስግደትን ፡ ጨምሬ (፪x)

ሰናክሬም ፡ ጦር ፡ አሰልፎብኝ
የማደርገው ፡ ምንም ፡ ሲጠፋኝ
የምሥጋና ፡ መዝሙር ፡ ለጌታ
ስዘምር ፡ ጠላቶቼን ፡ መታ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ
ለጌታ ፡ ስግደትን ፡ ጨምሬ

ሌሊቱን ፡ በሙሉ ፡ ስለፋ
አንድም ፡ የሚያዝ ፡ ዓሣ ፡ ጠፋ
ታንኳዬን ፡ ለጌታ ፡ ስሰጠው
መረቤን ፡ በዓሣዎች ፡ ሞላው

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ
ለጌታ ፡ ስግደትን ፡ ጨምሬ

ጳውሎስና ፡ ሲላስ ፡ በእስር ፡ ቤት
ተጥለው ፡ ሳሉ ፡ በእስራት
መዝሙር ፡ ሲዘምሩ ፡ ለጌታ
የእጃቸው ፡ ሰንሰለት ፡ ተፈታ

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ
ለጌታ ፡ ስግደትን ፡ ጨምሬ

ክፉ ፡ ሰልጥኖበት ፡ ሳዖል ፡ ላይ
አእምሮውን ፡ ስቶ ፡ ሲሰቃይ
ዳዊት ፡ በገና ፡ ሲደረድር
ክፉ ፡ መንፈስ ፡ ሸሸ ፡ ሲዘምር

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ
ለጌታ ፡ ስግደትን ፡ ጨምሬ

ሁሉን ፡ ለሚችለው ፡ ለኢየሱስ
በእምነት ፡ አስረክቦ ፡ መፈወስ
በምሥጋና ፡ ሆኖ ፡ መቆየት
ባርኮት ፡ ይመጣል ፡ ከፀባኦት

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዝማሬ (፪x)
ሰዋለሁ ፡ ላምላኬ ፡ እልልታን ፡ ጨምሬ
ለጌታ ፡ ስግደትን ፡ ጨምሬ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue