Amlake Amlake (አምላኬ ፡ አምላኬ)

አዝ፦ አምላኬ (፪x) ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ
ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እሮጣለሁ
ፊትህን ፡ አሳየኝ ፡ ደስታን ፡ እጠግባለሁ
ምህረትህ ፡ ይብዛልኝ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ

ገና ፡ ሌሊት ፡ ሳለ ፡ ከእንቅልፌ ፡ እነሳለሁ
የፊትህን ፡ ብርሃን ፡ ላይ ፡ እፈልጋለሁ
ነፍሴ ፡ እንደ ፡ ውኃ ፡ አንተን ፡ ትጠማለች
በቀንም ፡ በማታም ፡ ትናፍቅሃለች

አዝ፦ አምላኬ (፪x) ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ
ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እሮጣለሁ
ፊትህን ፡ አሳየኝ ፡ ደስታን ፡ እጠግባለሁ
ምህረትህ ፡ ይብዛልኝ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ

እጆቼን ፡ በሥምህ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እያነሳሁ
በዘወትር ፡ ፀሎት ፡ ምሥጋና ፡ አቀርባለሁ
በሁለንተናዬም ፡ እገዛልሃለሁ
ምንጊዜም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ በቤትህ ፡ እኖራለሁ

አዝ፦ አምላኬ (፪x) ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ
ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እሮጣለሁ
ፊትህን ፡ አሳየኝ ፡ ደስታን ፡ እጠግባለሁ
ምህረትህ ፡ ይብዛልኝ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ

ሺህ ፡ ዓመት ፡ በሥጋ ፡ ከመኖር ፡ በከንቱ
እውነትህን ፡ አውቆ ፡ ይሻላል ፡ መሞቱ
መስቀልህን ፡ መያዝ ፡ መርጫለሁ ፡ እኔ
ይህ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ የነፍሴ ፡ ውሳኔ

አዝ፦ አምላኬ (፪x) ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ
ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እሮጣለሁ
ፊትህን ፡ አሳየኝ ፡ ደስታን ፡ እጠግባለሁ
ምህረትህ ፡ ይብዛልኝ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue