Endalkachew Hawaz--Egzabher Tilk New--ታማኝ ፡ ነው

አዝ፦ ታማኝ ፡ ነው ፡ የተናገረውን ፡ የሚያደርግ
ቃልኪዳኑን ፡ የማይረሳ ፣ ቃልኪዳኑን ፡ የማይረሳ
ቸር ፡ ወዳጅ ፡ ምህረቱንም ፡ የሚያስብ
የሚደግፍ ፡ የሚያነሳ ፣ የሚደግፍ ፡ የሚያነሳ (፪x)
እኔም ፡ ስላየሁት ፡ በዘመኔ
አቀርብለታለሁ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ
ስሙን ፡ በምሥጋና ፡ አከብራለሁ
ሌላ ፡ ስለሌለኝ ፡ የምከፍለው (፪x)

ፍለጋውን ፡ እያስተማረ ፡ እካሄዴን ፡ እያሳመረ
መራኝ ፡ እኔን ፡ በድል ፡ ጐዳና
አረማመዴንም ፡ አጸና
ለስሙ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና (፬x)

ፍለጋውን ፡ እያስተማረ ፡ እካሄዴን ፡ እያሳመረ
መራኝ ፡ እኔን ፡ በድል ፡ ጐዳና
አረማመዴንም ፡ አጸና
ለስሙ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና (፬x)

አዝ፦ ታማኝ ፡ ነው ፡ የተናገረውን ፡ የሚያደርግ
ቃልኪዳኑን ፡ የማይረሳ ፣ ቃልኪዳኑን ፡ የማይረሳ
ቸር ፡ ወዳጅ ፡ ምህረቱንም ፡ የሚያስብ
የሚደግፍ ፡ የሚያነሳ ፣ የሚደግፍ ፡ የሚያነሳ (፪x)
እኔም ፡ ስላየሁት ፡ በዘመኔ
አቀርብለታለሁ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ
ስሙን ፡ በምሥጋና ፡ አከብራለሁ
ሌላ ፡ ስለሌለኝ ፡ የምከፍለው (፪x)

ነፍሴ ፡ በመልካም ፡ አደረች
የጌታን ፡ ቸርነት ፡ እያየች
ምህረቱን ፡ አግንኖልኛል
ከበጐነቱም ፡ አጥግቦኛል (፪x)
ባከብረው ፡ ይህ ፡ ያንስብኛል (፬x)

አዝ፦ ታማኝ ፡ ነው ፡ የተናገረውን ፡ የሚያደርግ
ቃልኪዳኑን ፡ የማይረሳ ፣ ቃልኪዳኑን ፡ የማይረሳ
ቸር ፡ ወዳጅ ፡ ምህረቱንም ፡ የሚያስብ
የሚደግፍ ፡ የሚያነሳ ፣ የሚደግፍ ፡ የሚያነሳ (፪x)
እኔም ፡ ስላየሁት ፡ በዘመኔ
አቀርብለታለሁ ፡ አዲስ ፡ ቅኔ
ስሙን ፡ በምሥጋና ፡ አከብራለሁ
ሌላ ፡ ስለሌለኝ ፡ የምከፍለው (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue