አቤቱ ፡ በዘመናት (Abietu Bezemenat)

አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል
ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ
ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ
ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x)

በዘመን ፡ በአመታት ፡ ስራህን ፡ እየሰራህ
የሚቃወምህ ፡ ሳይኖር ፡ ክንድህን ፡ እየገለጥክ
ልጆችህን ፡ ከድል ፡ ወደ ፡ ድል ፡ እያሸጋገርካቸው
የጠላታቸውን ፡ ሰፈር ፡ ይታያል ፡ . (1) . ፡ ወርሰው

አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል
ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ
ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x)

ፈርዖን ፡ ለዘመናት ፡ ሲያስጨንቅ ፡ ልጆችህን
ሕዝቤን ፡ ልቀቅ ፡ ስትለው ፡ ትዕቢት ፡ አርጐ ፡ ሲፋንን
በመጨረሻ ፡ ጌታ ፡ የግብጽን ፡ በኩር ፡ ገድለህ
ህዝብህን ፡ ነጻ ፡ አውጥተህ ፡ ጠላትን ፡ . (1) . ፡ ጥለህ

አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል
ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ
ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x)

ሁልጊዜ ፡ ሃሳብህን ፡ የልብህንም ፡ ፈቃድ
ታከናውነዋለህ ፡ በምትወደው ፡ መንገድ
በጐና ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ ነው
አምላካችን ፡ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ የምታደርገው

አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል
ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ
ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x)

ክብርህ ፡ ሰማያትንና ፡ ምድርን ፡ ሁሉ ፡ ሸፍኗል
በምክርህ ፡ በመንገድህ ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ያክልሃል
ውበትህ ፡ ከፀሐይ ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ እጅግ ፡ ይደምቃል
ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ይህን ፡ እያየ ፡ ያከብርሃል

አዝ፦ አቤቱ ፡ በዘመናት ፡ በአመታት ፡ መካከል
ብቻህን ፡ ስራህን ፡ ሰርተህ
ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ
ትኖራለህ ፡ ከብረህ ፡ ደምቀህ (፪x)

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

:: / ::
::
/ ::

Queue