Fitih Endetsehay yaberal (ፊትህ ፡ እንደፀሐይ ፡ ያበራል)

ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ ያበራል
እንደብዙ ፡ ውሆች ፡ ድምጽህም ፡ ያስፈራል
ግርማህ ፡የደመቀ ፡ ሞገስህ ፡ ልዩ ፡ ነው
እግርህ ፡ ስር ፡ ወድቄ ፡ እሰግድልህ ፡ አለሁ


አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ የዘለዓለም ፡ ጌታ
ሞትን ፡ ድል ፡ ያደረክ: ኃጢአትን ፡ የረታህ
ከወገን ፡ ከቋንቋ ፡ህዝቦችን ፡ የዋጀህ
ለአምላክህ ፡ መንግሥት ፡ ካህናት ፡አድርገህ
(ሰባቱን ፡ መጽሃፍት፡ ማህተም ፡ የፈታ
ውበትህ ፡ ያማረ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ) (፪x)

አዝ
ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ

ምስኪን ፡ ሆነህ ፡ መተህ ፡ ምስኪኑን ፡ ያከበርክ
ደሃ ፡ ሆነህ ፡ መተህ ፡ ደሃን ፡ ያበለጸክ
በደዌ ፡ ተመተህ ፡ ህምሙን ፡ የፈወስክ
ኃጢአትን ፡ ለብሰህ ፡ ሃጢያኑን ፡ ያነጻህ
(ድል ነስተህ ፡ በኃይልህ ፡ ባለድል ፡ ያረከን
አንተ ፡ አትጠገብም ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን) (፪x)

አዝ

ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ

ማምለጫ ፡ ቀዳዳ ፡ መሹለኪያ ፡ ሲጠፋ
ጐዳናው ፡እጅግ ፡ ጠቦ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲጋፋ
ችግር ፡ መፍታት ፡ አንተ ፡ ልማድህ ፡ ነውና
መጽሃፉን ፡ ገልጽህ ፡ ማኅተሙን ፡ ፈታህ
ጌታችን ፡(ኢየሱስ) ፡ ተባረክ ፡ ባለግርማ ፡ ሞገስ
ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ በዓለም ፡ ሁሉ ፡ ንገሥ

አዝ
ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ

Recently Listened by

0 comments
    No comments found

እዚህ ያስተዋውቁ!

Live Podcast

Sponsored Ads



:: / ::
::
/ ::

Queue